Get Mystery Box with random crypto!

በቄለም ወለጋ ዞን በመቻራ ወረዳ መንደር 20 ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ ወሎየ ሙስሊሞች ላይ አሰቃቂ ጭፍ | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

በቄለም ወለጋ ዞን በመቻራ ወረዳ መንደር 20 ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ ወሎየ ሙስሊሞች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ መፈጸሙ ተገለጸ
..
ሀሩን ሚዲያ፥ ሰኔ 27/2014
..
በቄለም ወለጋ ዞን በመቻራ ወረዳ መንደር 20 ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ ወሎየ ሙስሊሞች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ መፈጸሙ ተገለጸ። ቁስለኞች ሆስፒታል ማጨናነቃቸው የተገለጸ ሲሆን የሟቾች ቁጥር በርካታ መሆኑም ተገልጿል። የኦሮሚያ መጅሊስ ከጥቃቱ ከተረፉ ሰዎች ባጣራው መሠረት ገዳዮቹ ራሳቸውን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በሚል የሚጠሩ የሸኔ ጽንፈኛ ታጣቂዎች መሆናቸውን እንደነገሩት ገልጿል።
..
የኦሮምያ መጅሊስ ድርጊቱን አጥብቆ ያወገዘ ሲሆን መንግስት አስፈላጊውን የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ በአበክሮ ጠይቋል። በኦሮምያ ክልል በወለጋ የሚንሳቀሰው ይህ ቡድን ከቀናት በፊትም እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው ሙስሊም የጨፈጨፈ ሲሆን ዛሬ ድጋሚ ሙስሊም ወሎየዎችን በመንደራቸው መጨፍጨፉን የአካባቢው የአይን እማኞች እየገለጹ ይገኛሉ። ቡድኑ ከመንግስት የጸጥታ ሀይል ጋር አሁንም ድረስ በመዋጋት ላይ ይገኛል።
..
ሀሩን ሚዲያ


https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia