Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.85K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 17

2023-05-21 17:32:50
ማኀበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ፍቃድ በጊዜያዊነት ታገደ!!
#FastMereja
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያወጣውን ደብዳቤ ፋስት መረጃ ተመልክቷል በደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰው «ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ሰበር ዜና በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሚና ውጪ በሆነ አግባብ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያካሄደውን ስብሰባ የሚያውክና ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ መልዕክት ማሰራጨቱ ተረጋግጧል፡፡ ይህም የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን የሚተላለፍና በህገር ሁለንተናዊ ሰላም ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ነው፡፡

በመሆኑም ከጉዳዩ አጣዳፊነትና ሊያስከትለው ከሚችለው ጉዳት አንፃር በቀጣይ በባለሥልጣኑ ቦርድ ታይቶ ዘላቂ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ የጣቢያው ፈቃድ በጊዜያዊነት የታገደ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡»

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን
@fastmereja
5.5K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 14:29:06
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ በወረዳ 11 በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ።

አደጋው የደረሰው በወረዳ 11 አትክልት ተራ አከባቢ ሲሆን የ2 ሰዎች ህይወት አልፈዋል በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና መወሰዳቸውን ፋስት መረጃ ከወረዳው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja
5.7K views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 13:51:39
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አቶ አምሃ ዳኜውን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፣ የፓርቲው መስራች እና ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ እስክንድር ነጋ በትናንትና እለት "የአማራ ህዝባዊ ግንባር" የተሰኘ መመስረታቸው ተገልፇል።

@fastmereja
5.4K views10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 10:51:11 የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ጉዳትና ኪሳራ ማድረሱን መንግሥት ይፋ አደረገ
#FastMereja
በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም ማዕከሉን በትግራይ ክልል አድርጎ ለሁለት ዓመታት በተካሄደውና በሌሎች የተወሰኑ አካባቢዎች በነበረው ጦርነት፣ ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳትና ኪሳራ በአገር ላይ መድረሱን ገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ ተቋማቸው በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተካሄደው ጦርነት የደረሰውን ጉዳትና የመልሶ ግንባታ ፍላጎት የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት (Damage and Needs Assessment) በማከናወን፣ የጥናት ውጤቱን ለመንግሥት እንዳቀረበ ተናግረዋል።

በጥናት ግኝቱ መሠረትም ያጋጠመው አጠቃላይ ጉዳትና የኢኮኖሚ ኪሳራ በአጠቃላይ 28 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ሪፖርታቸው አመላክቷል። ይህም በወቅቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ነው።
ለቋሚ ኮሚቴው ያቀረቡት ሪፖርት ላይ ከተቀመጠው መረጃ መረዳት እንደተቻለው፣ ‹‹22 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 20.4 በመቶ የሚገመት ጉዳት›› ደርሷል።

በዚሁ ምክንያት የደረሰው የኢኮኖሚ ኪሳራ ደግሞ፣ ‹‹ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 5.5 በመቶ የሚገመት የኢኮኖሚ ኪሳራ (Economic Loss)›› መድረሱን ሪፖርቱ ያመለክታል።
ግጭትና ጦርነት በነበረባቸው አካባቢዎች ከሚገኙ ጠቅላላ ነዋሪዎች ውስጥ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት በጦርነቱ በቀጥታ የተጎዱ መሆናቸውን፣ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ሦስት ሚሊዮን የሚሆኑት የአገሪቱ ዜጎች በጦርነቱ ምክንያት የከፋ ድህነት ውስጥ መግባታቸውንም አስረድተዋል።

ሚኒስትሩ ባቀረቡት ሪፖርት የተቀመጠው የጉዳት መጠን፣ ኢትዮጵያ ባለፉት በርካታ ዓመታት ከውጭ አበዳሪዎች ለኢኮኖሚ ልማት ተበድራ ካልመለሰችው አጠቃላይ የውጭ ዕዳ ጋር እኩል መሆኑን መረዳት ይቻላል። የገንዘብ ሚኒስቴር በየሩብ ዓመቱ ይፋ በሚያደርገው የዕዳ ሁኔታ መግለጫ መሠረት፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያለባት አጠቃላይ የውጭ ዕዳ መጠን 28 ቢሊዮን ዶላር ነው።

ዘገባው የሪፖርተር ነው

@fastmereja
5.7K views07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:39:27
አርሰናል ማል ታቴ? ሲቲ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ሻምፒዮን መሆኑ ታወቀ!
#FastMereja
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ለረጅም ጊዜ ሲመራ የነበረው አርሰናል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሪነቱን ለማንችስተር ሲቲ አስረክቦ ከዋንጫ መሸሹ በርካቶችን አስገርሟል። ከብራይተን ሽንፈት ማገገም ያልቻሉት አርሰናሎች ዛሬም በኖቲንግሃም ፎረስት 1 ለ 0 ተሸንፏል። ማንችስተር ሲቲ ነገ ሳይጫወት የዋንጫው ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል።

@fastmereja
6.4K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:24:53 በቀን እስከ 35ሺ ብር የሚቆጥቡ ሿሿ ሰሪዎች
#FastMereja
ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ወንጀል ፈፃሚዎቹ በቀን እስከ 35ሺ ብር ተቀማጭ  እንደሚያደርጉ በምርመራ ተረጋግጧል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብን ለምሬት ከዳረጉ የወንጀል ድርጊቶች መካከል በተለምዶ ሿሿ የሚባለው ወንጀል አንዱ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀሉን ለመከላከል እና ወንጀለኞቹን ህግ ፊት ለማቅረብ በጥናት ላይ ተመስርቶ ባከናወነው ተግባር በተለያዬ ክፍለ ከተሞች ወንጀሉን ሲፈፅሙ የነበሩ 25 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ አያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ኃይል በመጠቀም ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አንበሳ ጋራዥ አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኦሮ 86853 ነጭ ሚኒባስ በመጠቀም ከአንድ ግለሰብ ላይ 10ሺ ብርና ግምቱ 14 ሺብር የሚወጣ ሞባይል ስልክ ሰርቀው ይሰወራሉ፡፡ ፖሊስ ጠንካራ  ክትትል  በማድረግ ወንጀል ፈፃሚዎቹን ከእነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር በማዋልና ምርመራ በማስፋት ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የሚፈፅሙ 14 ወንጀል ፈፃሚዎችን እና  የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ኦሮ 79184 ሚኒባስ ተሽከርካሪን ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ /ም ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ረዳት ኮሚሽነር ፋሲካ ፋንታ አስታውቀዋል፡፡

ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ግለሰቦች በቦሌ ክፍለ ከተማ 6 ቦታዎች ፣ በየካ ክፍለ ከተማ 3 ቦታዎች እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 3 ቦታዎች ላይ ወንጀሉን መፈፀማቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

አቶ በሪሁን ካሳው ይባላሉ የአዲስ አበባ ነዋሪ ናቸው፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስፍራው ዘሪሁን ህንፃ አከባቢ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ/ም ግምቱ 10ሺ ብር የሚያወጣ  ሞባይል ስልክ በወንጀል ፈፃሚዎች  የተሰረቀባቸው  ቢሆንም ፖሊስ ንብረተቻውን ማስመለሱን ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ አቶ አበበ በቀለ ወደ ስራ በመሄድ ላይ እያሉ በእነዚሁ ወንጀል ፈፃሚዎች ግምቱ 10ሺ ብር የሚያወጣ ስልክ መሰረቃቸውን እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል በተሰረቁ ጥቂት ሰዓት ውስጥ ወንጀል ፈፃሚዎቹ ተይዘው  ንብረታቸው መገኘቱን አስረድተዋል፡፡

በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ ያላቸው 19 ወንዶችና 6 ሴቶች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ሁለት ሚኒ-ባስ መኪናዎች እንዲሁም ግለሰቦቹ ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚጠቀሙባቸው 4 ልዩ ልዩ ተሸከርካሪዎች ፣ 82 ሺ 680  ጥሬ ብር ፣ 14 ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ስማርት ስልኮች እና የቀን ተቀማጭ የሚያስቀምጡበት ደብተር በኤግዚቢትነት እንደተያዘ ረዳት ኮሚሽነር ፋሲካ ፋንታ አስረድተዋል፡፡

ግለሰቦች ምንም አይነት ህጋዊ ገቢ የሚያገኙበት ስራ የሌላቸው ቢሆንም ከፍተኛው በቀን 35 ሺ ብር አነስተኛው 5ሺ ብር የቀን ተቀመጭ ሲያደርጉ እንደነበር  በኤግዚቢትነት ከተያዘው ሰነድ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የተፈፀመባቸው ግለቦች አዲስ አበባ ፖሊስ  ጉለሌ ክፍለ በመቅረብ በኤግዚቢትነት ከተያዙ ስልኮች መካከል መምረጥ እንደሚችሉ ረዳት ኮሚሽነር ፋሲካ አስታውቀዋል፡፡

በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን ወንጀል የሚፈፅሙ ወንጀለኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው ወንጀሉን እንደሚፈፅሙ እና መነሻና መድረሻ የሌላቸው ሲሆኑ  ተሳፋሪውን የትነው የምትሄደው የሚል ጥያቄ እንዲሚያቀርቡ ህብተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደለበት ኃላፊው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፇል።

@fastmereja
6.3K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:24:26
5.4K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:05:19
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ ተወሰደ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ ግንቦት 12፤ 2015 ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ መወሰዱን የዓይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ተመስገንን የወሰዱት በሁለት ፒክ አፕ ተጨነው የመጡ እና የፖሊስ ደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ኃይሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

እስከ ምሽት ድረስ ከቅርብ ጓደኞቹ የነበረው ተመስገን፤ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በሚገባበት ወቅት፤ የግቢ ዙሪያው በጸጥታ ኃይሎች ተከብቦ ማግኘቱን የዓይን እማኞቹ ተናግረዋል።

ምንጭ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@fastmereja
6.1K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 14:40:14
የሟቾች ቁጥር 20 ደረሰ!!
#FastMereja
የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው መኪና በደረሰበት አደጋ በአሁኑ ወቅት የሟቾች ቁጥር 20 መድረሱ ተገለፀ። አደጋው የደረሰው መምህራኑ ሻሸመኔ ካምፓስ ለማስተማር ወደ ዶዶላ እየተጓዙ እያሉ በም/አርሲ ዋሻ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መኪናው መንገድ ስቶ ገደል ውስጥ በመግባቱ መሆኑን ለፋስት መረጃ የደረሰው መልዕክት ያመላክታል። የቀሩት አዳባ፣ ዶዶላ እና ሮቤ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

@fastmereja
6.8K views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 12:20:49 15 የዩንቨርሲቲ መምህራን በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ
#FastMereja
የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰው የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡

የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ንጋቱ ሞቱማ ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ እስካሁን 15 የዩንቨርሲቲው መምህራን ህይወት ማለፉን ገልፀዋል ሲል ኦቢኤን ነው የዘገበው።

@fastmereja
6.9K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ