Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ አሪ ወረዳ አርሶ አደርና በሳላማጎ ወረዳ አርብቶ አደር መሃል በተፈጠረዉ ግጭት ምክንያት ለ | FastMereja.com

በደቡብ አሪ ወረዳ አርሶ አደርና በሳላማጎ ወረዳ አርብቶ አደር መሃል በተፈጠረዉ ግጭት ምክንያት ለሞቱ 8 ሰዎች ከደቡብ አሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የተሰጠ መግለጫ

በደቡብ አሪ ወረዳ አርሶ አደርና በሳላማጎ ወረዳ አርብቶ አደር መሃከል በተፈጠረዉ ግጭት ምክንያት እስካሁን 7 የደቡብ አሪ ወረዳ አርሶ አደርና 1የዳሰነች ወረዳ ጸጥታዉን ለማረጋጋት የመጣ የፓሊስ አባል በሳላማጎ ወረዳ አርብቶ አደሮች ተገድለዋል።

ግጭቱ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ሰዎች እየሞቱና የአካባቢዉ ሰላም ጠፍቶ ዘጎች በስጋት ዉስጥ መግባታቸዉን በመገንዘብ መንግስት ለማረጋጋት እየሰራ መሆኑ ይታወቃል በዝህም መሰረት የደቡብ አሪ ወረዳ ጸጥታ ኃይል የአጎራባች ወረዳዎች የፖሊስ አባላትና የክልሉ የጸጥታ ኃይል አብሮ በመተባበር ስያረጋጉ ከቆዩት አንዱ የዳሰነች ወረዳ ፓሊስ አባል ኮንስታብል ዮሐንስ ሎቱሊያ እና 7 አርሶ አደሮች በግጭቱ ምክንያት መሞታቸዉ ተገልጿል።

በመሆኑ የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዳልቅ አልቅሚ እስካሁን ለሞቱት የወረዳችን አርሶ አደር ቤተሰቦችና የፓሊስ አባሉ ቤተሰቦች እንድሁም ለዳሰነች ወረዳ መንግስትና አጠቃላይ የሁለቱ ወረዳ ህዝቦች መጽናናትን ይመኛል።

እንደዝህ አይነት የእርስ በርስ ግጭቶች የዜጎች ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳትና የህይወት እልቅትን የሚያስከትል በመሆኑ ሰዉ ከግጭት ይልቅ ችግርን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንድችል በመግለጽ በድጋሚ ለሟች ወዳጅ ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን ብለዋል።

@fastmereja