Get Mystery Box with random crypto!

በሚኒባስ ተሽከርካሪ ውስጥ ባዶ ፍራሽ አንጥፈው የኩላሊት ታማሚ የተኛ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገ | FastMereja.com

በሚኒባስ ተሽከርካሪ ውስጥ ባዶ ፍራሽ አንጥፈው የኩላሊት ታማሚ የተኛ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ግለሰቦቹ የማታለል ድርጊቱን ሲፈፅሙ የተገኙት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሲኒማራስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው አራት ተጠርጣሪዎች የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 43018 አ.አ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ውስጥ ባዶ ፍራሽ በማንጠፍ ፣ በፍራሹ ላይ የኩላሊት በሽታ ታማሚ የተኛ በማስመሰል እና የግለሰብ ፎቶ በባነር አሳትመው በመስቀል በስፒከር እየቀሰቀሱ በህክምና ወጪ ሰበብ ከህብረተሰቡ ገንዘብ ሲሰበስቡ የፖሊስ አባላት በጥርጣሬ ባከናወኑት የማረጋገጥ ስራ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል፡፡

መደጋገፍና መረዳዳት ከኢትዮጵያውያን መገለጫዎቻችን አንዱ ቢሆንም በአቋራጭ ለመበልፀግ ህብረተሰቡን በማታለል እንዲህ አይነት ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን በመገንዘብ እውነተኛ ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎችን ማገዝ እንደተጠበቀ ሆኖ በህክምና ሰነዶች እና በሌሎች ሁኔታዎች የማረጋገጥ ስራ በመስራት አታላዮችን ማጋለጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

@fastmereja