Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ ይከናወ | FastMereja.com

በኦሮሚያ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ ይከናወናል።
#FastMereja
ኔትወርክ በሌለበት አካባቢም ሲ ቢ ኢ ብር በመጠቀም ይቻላል ተብሏል።

በኦሮሚያ ክልል ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንደሚከናወን የክልሉ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በኤሌክትሮኒክስ የሚከነወነው የነዳጅ ግዥና ሽያጭ የተሳለጠ እንዲሆንም የሚመለከታቸው አካላት ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆኑ ሲል ቢሮው አሳስቧል፡፡

በሌላ በኩል እንደ አቢሲያ ካርድ ኩፖን እና ሌሎች የግብይት መፈጸሚያ ዘዴዎች ሲጠቀሙ የነበሩ ተቋማት እስከያዝነው በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ብቻ መጠቀም እንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡

ኔትወርክ በሌለበት አካባቢም ሲ ቢ ኢ ብር በመጠቀም የነዳጅ ግብይት መፈጸም እንዲቻል ከቴሌ ጋር ስምምነት ላይ ተደርሶ መተግበሪያው መበልጸጉን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

@fastmereja