Get Mystery Box with random crypto!

ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ያኮረፈዉ ወጣት እራሱን አጠፋ #FastMereja በደቡብ ክል | FastMereja.com

ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ያኮረፈዉ ወጣት እራሱን አጠፋ
#FastMereja
በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ከቤተሰቦቹ ተጨቃጭቆ መግባባት ያልቻለዉ ወጣት በገመድ እራሱን ሰቅሎ ህይወቱን ማጥፋቱ ፖሊስ አስታዉቋል።

በደቡብ አሪ ወረዳ ባላመር ቀበሌ ነዋሪ የሆነዉ ይህ ወጣት ለ2015 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል ልብስ እንዲገዛለት ለወላጆቹ ጥያቄ ማቅረቡ ተከትሎ ወላጆቹም ቀደም ሲል የሚለብሳቸዉን ልቦሶች አፅድቶ በመልበስ የዘንድሮዉን በዓል አክብሮ እንዲዉልና በሱ ጥያቂነት ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቤተሰብ አልባሳት ይገዛልሀል የሚል ተስፋ አስቆራጭ ምላሽ ይሰጠዋል። ወጣቱ በወላጆቹ እምቢታ ተናዶ እራሱን እንደሚያጠፋ ዝቶ ከቤተሰቦቹ ጋር ከስምምነት ሳይደርስ መለያየቱ ነዉ ከፖሊስ በደረሰን መረጃ ለመረዳት የተቻለዉ።

ወጣቱ እራሱን ለማጥፋት ቢዝትም ቤተሰብ እንዲህ አይነቱ እኩይ ተግባር ሊፈፅም ይችላል የሚል ጥርጣሬ አልነበረዉም ተብሏል።ነገር ግን ሚያዝያ 08 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 12:00 ሰዓት ላይ ወጣቱ እራሱን በገመድ ሰቅሎ በድን ገላዉ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ እንደተገኘና የወጣቱ አድራጎት ቤተሰቡን በእጅጉ ያስደነገጠና ያሳዘነ ሆኖ ማለፉ ነዉ ፖሊስ ያስታወቀዉ።

ሁለት ወራትን በፆም በፀሎት የከረሙት የሟች ቤተሰቦች የፋሲካን በዓል ለማክበር ያልታደሉ ሆነዉ ድንኳን ቀስተዉ የልጃቸዉ ሀዘን ለመቀመጥ ተገደዋል ሲል ከደቡብ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja