Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ጓደኛዬ ፂሜን አይቶ ነው የወደደኝ አያንቱ አድማሱ ትባላለች ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ በእንስሳት | FastMereja.com

የፍቅር ጓደኛዬ ፂሜን አይቶ ነው የወደደኝ

አያንቱ አድማሱ ትባላለች ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ በእንስሳት ህክምና ተመርቃለች። ተወልዳ ያደገችው በቄለም ወለጋ በዳምቢ ዶሎ ነው። አያንቱ ወደ ጉርምስና ከገባችበት ጊዜ ጀምሮ ከልጃገረዶች የተለየ ነገር ማየት ጀመረች፣ እንደ ወንድ ፂም ማብቀል ጀመረች።

ሳይንሳዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሴቶች እንደ ወንድ ጢም ማብቀል የተለመደ ባይሆንም አልፎ አልፎ እንደሚከሰት ይገለፃል።

አያንቱ በልጅነቷ መላ ሰውነቷ በፀጉር ተሸፍኖ እንደነበር እና ካደገች በኋላ እንደጠፋላት ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልፃለች። "ቤተሰቦቼ በልጅነቴ በሰውነቴ ላይ ብዙ ፀጉር ነበረኝ ይላሉ፣ በኋላ ላይ ጠፋ እና ወደ ጉርምስና ስገባ ፂም መብቀል ጀመረ" ብላለች።

መጀመሪያ ላይ ፊቷ ላይ ፂም ሲወጣ ስታይ ተናዳ እራሷን ጠልታ እንደነበር ገልፃለች።

የፍቅር ጓደኛዋ ፂሟን ወዶላት ለፍቅር እንደጠየቃት ትናገራለች "ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ እንዳልቆረጥ ያበረታታኛል" ስትል ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ሃሳቧን አካፍላለች።

@fastmereja