Get Mystery Box with random crypto!

መንግስት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን እስር እና እንግልት ያቁም ! የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎ | FastMereja.com

መንግስት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን እስር እና እንግልት ያቁም !

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ወገንተኝነታቸው ለህዝብና ለእውነት መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም በስራቸው ላይ ስህተት በሚሰሩበት ወቅት ደግሞ በህግ አግባብ መጠየቅ እንዳለባቸው እና የህግ የበላይነት መከበር እንዳለበት ማህበራችን በፅኑ ያምናል።

ይሁን እንጅ " ከለውጡ በኋላ " በሀገራችን የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት እንዲረጋገጥ ማህበራችን ብዙ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ባለሙያዎች የሚሰሩበት አውድ እየጠበበ ጋዜጠኞች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ በመንግስት የፀጥታ አካላት እየተሸማቀቁ እና እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ማህበራችን እየታዘበ ነው።

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር መስራችና የስራ አስፈፃሚ አባል እንዲሁም የማህበራችን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን ጨምሮ አራጋው ሲሳይ ፣ ገነት አስማማው ፣ ጌትነት አሻግሬ ፣ በየነ ወልዴና ቴዎድሮስ አስፋው በመንግስት ሀይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ። አንዳንዶቹም ያሉበት ቦታ እና ምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንኳን ቤተሰቦቻቸውም በቂ መረጃ ሳይኖራቸው በእስር ላይ ይገኛሉ።

ጋዜጠኞች ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ እየታሰሩ፣ እየታፈኑና ቤታቸውና ቢሯቸው እየተበረበረ መሆኑ ባለሞያዎች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ፤ የፕረስ _ ምህዳሩ _ የበለጠ እንዲጠብ እያደረገ ነው። ማህበራችንም የተቋቋመው እንደዚህ አይነት ሙያውን የሚያቀጭጩ ጫናዎችን ለመታገል በመሆኑ እርምጃዎችን በፅኑ ያወግዛል።

ሙሉ መግለጫው ተያይዟል…

@fastmereja