የአሮጌው ብር የመገበያያ ጊዜ ከነገ ጀምሮ ያበቃል የአሮጌው ብር ኖት የመገበያያ ጊዜ ከነገ ህዳር | FastMereja.com
የአሮጌው ብር የመገበያያ ጊዜ ከነገ ጀምሮ ያበቃል
የአሮጌው ብር ኖት የመገበያያ ጊዜ ከነገ ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያበቃል።
የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል።
ባንኩ ከዚህ ቀደም ህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ከነገ ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት አይቻልም።
ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።
የብር ኖት ቅያሬው በሶስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መወሰኑም አይዘነጋም።
-------------
@fastmereja