Get Mystery Box with random crypto!

የአለማችን ተጠቃሽ የኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች የ'ሆን ዞ' አውቶ ፋክተሪ የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍ | FastMereja.com

የአለማችን ተጠቃሽ የኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች የ"ሆን ዞ" አውቶ ፋክተሪ የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ወኪል ኢትዮፒካር ብራንድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በብድር አስረከበ።

መኪኖቹ የግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባል የሆኑና 30% ቁጠባን ለቆጠቡ ነው የተሰጠው። በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖች በበርካታ ሃገራት ተመራጭነታቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ይገኛል ኢትዮጵያም እንደ ሃገር የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ብሎም የአየር ንብረትን ለመጠበቅ ይረዳ ዘንድ የኤሌክትሪክ መኪናን እንደ አማራጭ የመጠቀም ፓሊሲን ከመተግበር ባለፈ በሃገራችን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት ከፍተኛ እየሆነ መጥቷል።

ይህንን ፖሊሲ እና የተጠቃሚዎች ፍላጎት ከግምት በማስገባት የአለማችን ተጠቃሽ የኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች የሆነው የ"ሆን ዞ" አውቶ ፋክተሪ የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ወኪል ኢትዮፒካር ብራንድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ለተጠቃሚዎች እያቀረበ ይገኛል።

የዜጎችን ኑሮ ባማከለ መልኩ በባንክ ብድር አማራጭ እየቀረቡ የሚገኙት እነዚህ የኤሌክት መኪኖች የፋብሪካ ዋስትና ያላቸውም ናቸው።

ለዚህም በዛሬው ዕለት ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ኢትዮፒካር ብራንድ ከግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም ጋር የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለተቋሙ አባላት በብድር መስጠት የሚያስችል ስምምነት ፈፅሟል፡፡
 
በዚህ ስምምነት መሰረትም የ"ሆን ዞ" አውቶ ፋክተሪ የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ወኪል ኢትዮፒካር የግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባላት የሚፈልጓቸውን የኤሌክትሪክ መኪኖች ምቹ እና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ በብድር  እንደሚሰጥ ''የኢቲዮፒካር'' ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል አዲስአለም  ገልፀዋል።

  በተጨማሪም ዛሬ ግንቦት 29/2016 ዓም  ኢትዮፒካር የግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም አባላት ለሆኑና የብድር መስፈርቱን አሟልተው 30 በመቶ ቁጠባ ለፈፀሙ አባላት የኤሌክትሪክ መኪኖችን አስረክቧል።

  ባለፉት ዓመታት በሃገራችን በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ብሎም የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎችን ከተለያዩ ሃገራት በማስመጣት ለደንበኞቹ ሲያቀርብ የቆየው ድርጅታችን ከዚህ ቀደም ከባንኮች ጋር በመሆን ከአርባ በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች በኤሌክትራክ የሚሰሩ መኪኖችን ማስረከቡ ይታወሳል።