Get Mystery Box with random crypto!

በወላይታ ዞን 75 አመራሮች ላይ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተገኘ #FastMereja በወላይታ | FastMereja.com

በወላይታ ዞን 75 አመራሮች ላይ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተገኘ
#FastMereja
በወላይታ ዞን ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ የተገኙባቸው 75 አመራሮች ላይ ፖለቲካዊ ፣ህጋዊና አስተዳዳራዊ እርምጃ መወሰዱን የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ አስታውቋል።

በወላይታ ዞን 1079 አመራሮች የትምህርት ማስረጃ ተፈትሾ75 አመራሮች የትምህርት ማስረጃቸው ፎርጅድ ስለ መሆኑ መረጋገጡን ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን የተናገሩት የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ፀጋ ፋንታ ናቸዉ፡፡120 የሚሆኑ አመራሮች የትምህርት ማስረጃ ያገኙባቸው ተቋማት በአሁኑ ሰዓት ሥራ ያቆሙ በመሆናቸው ማስረጃቸውን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ እንዲጣራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በቀሪ አመራሮች የትምህርት ማስረጃ ማጣራቱ ተጠናቆ በሚገኙ ግኝቶች መነሻ ተመሳሳይ የእርምት እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማጣራት፥ ህጋዊ እርምጃ በመወሰድ የመንግስትና የህዝብ ሀብት ማዳን ላይ ዞኑ በትኩረት እየሰራ ነው ተብሏል።

በየተቋማት ሥር ከሰደዱ ችግሮች ውስጥ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ዋናው መሆኑን የተናገሩት ወይዘሮ ፀጋ ይህንንም በማጣራት፥ ህጋዊ እርምጃ በመወሰድ የመንግስትና የህዝብ ሀብት ማዳን በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል። ባልተፈቀደና ባልተቀረጸ መደብ ላይ የተፈጸሙ ቅጥሮች የተሰጡ ምደባዎችና የደረጃ ዕድገቶች በአስቸኳይ ሊታረሙና እነዚህን ብልሽቶች የፈጸሙ እንዲሁም በህገወጥ ተግባራት ላይ የተሳተፉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰድ እንደሚገባም ተመላክቷል።

ዘገባው የብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ነው።
****
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja