Get Mystery Box with random crypto!

የአስፓልት መንገድን በአፈርና በጠጠር አንዲሁም በጭቃ ያበላሹ 91 የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ተቀ | FastMereja.com

የአስፓልት መንገድን በአፈርና በጠጠር አንዲሁም በጭቃ ያበላሹ 91 የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ተቀጡ
#FastMereja
በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አምስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የጫኑትን ጭነት ሳይሸፍኑ እንዲሁም የተሸከርካሪ ጎማ ሳያጸዱ በማሽከርከር በመንገድ ላይ ጠጠርና አፈር ያንጠባጠቡና በጭቃ አስፓልት ያበላሹ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን በልዩ ኦፕሬሽን እንዲቀጡ አድርገዋል፡፡

በተለይም በ90 ቀናት የተግባር ክንውን ወቅት የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ አፈርና ጭቃ ከጎማ ላይ ሳያፀዱ ወደ መንገድ እንዳይወጡ እንዲሁም ከመጠን በላይ ትርፍ አፈርና ቆሻሻ እንዳይጭኑ ተገቢውን ቁጥጥር እዲደረግ በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት በየቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከ ግንቦት 1 እስከ 10 ባሉት ቀናት በለሚ ኩራ 38 በቦሌ 36 በአዲስ ከተማ 7 በልደታ 4፣ በቂርቆስ 4 በየካ 2 በድምሩ 91 አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል፡፡

በአጫጫን ጥንቃቄ ጉድለት ጭነትን ሳይሸፍኑ ያንጠባጠቡ እና ከተሸከርካሪዎች ጎማ ላይ ጭቃ ሳያጸዱ አስፓልት መንገድን ያበላሹ እነዚሁ አሽከርካሪዎች የተቀጡት በደንብ 395/2009 በእርከን 1/14 መሰረት ሲሆን ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትራፊክ ማኔጅመንት አስታውቋል።
****
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja