Get Mystery Box with random crypto!

'ፖሊሱ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ነው' የአፋር ፖሊስ #FastMereja በማህበራዊ ሚዲያዎች | FastMereja.com

"ፖሊሱ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ነው" የአፋር ፖሊስ
#FastMereja
በማህበራዊ ሚዲያዎች የከባድ መኪና ሹፌር በማስቆም ሲያስፈራራ እና ሲያንገላታ የሚታየው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርምራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ቢልኤ አህመድ ገልጸዋል።

ይህ አሽከርካሪ ላይ በግድ መንገደኛ የመጫን ተግባር ከፖሊስ ዲሲፕሊን ውጭ የሆነ ተግባር በመሆኑ የአፋር ክልል ፖሊስ ጉዳዩን በማጣራት ተመጣጣኝ የሆነ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማረጋገጣቸውን ፋስት መረጃ ከአፋር ፖሊስ ያገኘው ሰምቷል።

ኮሚሽነር ጄነራሉ ይህ ተግባር የህዝብ ልጅ እና በህዝባዊ ወገንተኝነቱ የሚታወቀው የአፋር ፖሊስ እንደማይወክል አሰረድተዋል።
****
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja