Get Mystery Box with random crypto!

በዲላ ዙሪያ ወረዳ የጅብ መንጋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ መጠጥ ቤቶች እስከ 12 ሰዓት ብቻ እንዲሰሩ | FastMereja.com

በዲላ ዙሪያ ወረዳ የጅብ መንጋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ መጠጥ ቤቶች እስከ 12 ሰዓት ብቻ እንዲሰሩ ፖሊስ አስጠነቀቀ።
#FastMereja
ከዚህ በፊት ባልተለመደው መልኩ በዲላ ዙሪያ ወረዳ አንዳንድ አከባቢዎች የጅብ መንጋ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የገለጹት የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ም/ኢ/ር መሰለ ወንዱ ጀጎ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ም/እ/ር ይህንን ያሉት በሽጋዶ ቀበሌ ልዮ ቦታ ባፋኖ ተብለው በሚጠራበት አከባቢ ነዋር የሆኑት አቶ አለማዬሁ ጎበና የተባሉ ግለሰብ ግንቦት 11/2016 ዓ/ም አምሽተው ወደ ቤታቸው ስመለሱ በጅብ መንጋ መበላታቸውን በገለጹበት ወቅት ነው፡፡

አቶ አለማየሁ ወደ ቤት ሳይመለሱ በመቅረቱ ቤተሰቦች ፍለጋ በወጡበት ወቅት በመንገድ ላይ ልብስ ጫማና የተለያዩ የሰውነት ክፍል የቀሩ ስጋና አጥንት በማግኘታቸው ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሠረት ፖሊስ ባደረጉት ምርመራ ባገኙት ምልክቶች ግለሰቡ በጅብ መበላታቸውን ማረጋገጣቸው የገለጹት አዛዡ በአከባቢው ከፍተኛ የጅብ ጩሄት እንደነበረው ከአከባቢው ማህበረሰብ ማረጋገጥ መቻሉን አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ የትኛውን ማህበራዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ከገበያ በሚመለሱበት ወቅት በጊዜ ወደ የቤታቸው መመለስ እንዳለበት በመግለጽ በም/ቤቱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ማነኛውም መጠጥ ቤቶች እስከ ምሽቱ 12:00 ስዓት ብቻ መሆኑን ገልጸው ከዚህ ውጭ በሆኑ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግሯል፡፡

የጅብ መንጋ እንቅስቃሴ ስጋት በመጨመሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በጊዜ ወደየ ቤታቸው መግባት እንደለበትና ልጆች የቤት እንስሳትን ስጠብቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና ወደ ጫካ ውስጥ እንዳይሄዱ አሳስቧል።

በመጨረሻ በአካባቢው ለረዥም ጊዜያት ጅብ እንደነበሩ የገልጹት ም/እ/ር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በአጎራባች ቀበሌያት መሠል ጥቃት መድረሱን በማንሳት ማህበረሰቡ በጊዜ በመግባት የሚሰጠዉን የጥንቃቄ መልእክት በአግባቡ እንዲተገብርም ጠይቀዋል።

ዲላ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ ጽ/ቤት
****
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja