Get Mystery Box with random crypto!

በዚፕ ቁልፍ ሚመጣ የብልት አደጋ ------- የውንድ ልጅ ብልት አካባቢ ከሚደርሱ አደጋዎች ዋነኛው | FastMereja.com

በዚፕ ቁልፍ ሚመጣ የብልት አደጋ
-------
የውንድ ልጅ ብልት አካባቢ ከሚደርሱ አደጋዎች ዋነኛው በሱሪ መዝጊያ ዚፕ የሚመጣ ነው። ይህ ደሞ በብዛት ህፃናት ወንዶች ላይ ተደጋግሞ ይታያል። ለዚህም የህፃናት ልጆች ሃሳብ ወደጨዋታ በመሳብ ላይ ሆኖ ዚፕ ለመክፈት ወይም ለመዝጋት በሚያደርጉት ሙከራ ተደጋግሞ ይከሰታል።

በዚህም ምክንያት ህመም፣ ማበጥ፣ መድማት ከፍ ካለም ቆዳ ውስጥ ገብቶ መቀርቀርን ያመጣል። ቶሎ ካልታከመ ደግሞ ብዙ ጥሩ ያልሆኑ እና ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥሉ መዘዞችን ያመጣል።

በዚህ ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ደሞ ቤተሰብ ወይም አሳዳጊ ይህን ሁኔታ ለማስተካከል ሆስፒታል ከመምጣቱ በፊት እዛው ይታገላል። ይህም ለተጨማሪ ስቃይ፣ ጉዳት እና ቶሎ ወደ ሃኪም ቤት ከመሄድ መዘግየትን ይዳርጋል።

ስለዚህ ቤተሰብ ለህፃናት ወንድ ልጆቻችሁ ዚፕ የመክፈትን እና የመዝጋትን ነገር ብትከታተሉና ብታግዙ ሁኔታው ከተፈጠረ ደግሞ ቶሎ ወደጤና ተቋማት ብታመጧቸው ይመከራል።

ዶክተር መላኩ አባይ (Pathologist)
****
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja