Get Mystery Box with random crypto!

«በስቃይ እና መከራ ነው ያደኩት፣ ጓደኞቼ ሲዝናኑ እኔ እንጀራ እሸጥ ነበር፣ ዘመዶቼ እናቴ እና ል | FastMereja.com

«በስቃይ እና መከራ ነው ያደኩት፣ ጓደኞቼ ሲዝናኑ እኔ እንጀራ እሸጥ ነበር፣ ዘመዶቼ እናቴ እና ልጆቼ ናቸው!» አቶ ከድር ጁሃር
#FastMereja
ከደሃ ቤተሰብ ነው የወጣውት ይለሉ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ከሰይፉ ጋር በነበራቸው ቆይታ "እንጀራ እሸጥ ነበር አባቴ ሌላ ሚስት ሲያገባ ኑሮ አስቸጋሪ ሆኖብን ነበር ጓደኞቼ ሲጫወቱ ሲዝናኑ እኔ እናቴን ለማገዝ ብዬ ቤት ውስጥ ቀርቼ ነበር ብለዋል።

ከእንጀራ ውጪ ሴቶች የሚሰሩትን ጠቅላላ ነገር ሰርቻለሁ የሚሉት አቶ ከድር ጁሃር ይህ ሁሉ የተከሰተው አንድ ቀን እናቴ የኛ ያልሆነ ልብስ ስታጥብ አገኘዋት ይህ ልብስ የማነው ስላት ጎረቤቶቼን ላግዝ ብዬ ነው አለችኝ ግን 20 ብር ሲሰጧት አየሁ ከዛ ቀን በኋላ እናቴ መስራት የለባትም የሚል አቋም ይዤ እኔ መስራት ጀመርኩ ይላሉ። የመጨረሻ እህቴ ስትወለድ እኔ ነኝ ገንፎ እየሰራው ያረስኳት ብለዋል።

«ትናንት እናቴን ብዙ ችግር ስታሳልፍ አንድም ዘመድ ዞር ብሎ አላየንም፣ አሁን ስልጣን ስይዝ ብዙ ሰው መጥቷል እኔ አይገባኝም፣ አሁንም ዘመዶቼ እናቴ እና ልጆቼ ናቸው፣ ነገ ከስልጣን ብወርድ ፊታቸውን ስለሚያዞሩብኝ የሚያዋጡኝ ቤተሰቦቼ ናቸው» ብሏል።