2022-05-14 13:15:48
ወደ ውጪ መላክ የነበረበት ከ235 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ እህል በክምችት መኖሩ ተረጋገጠ
ግንቦት 5/2014 (ዋልታ) ወደ ውጪ መላክ የነበረበት ከ235 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ የጥራጥሬ እና የቅባት እህል በክምችት መኖሩ መረጋገጡን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ሚኒስቴሩ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአራት ከተሞች በክምችት ተይዘው የሚገኙ የቅባትና ጥራጥሬ ሰብሎች በአይነትና በመጠን ለማጣራት ዳሰሳዊ ጥናት አካሂዷል።
በተደረገው የዳሰሳ ጥናትም፦
- በአዳማ ከተማ 6 ሺሕ 610 ነጥብ 18 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል እንዲሁም 55 ሺሕ 485 ነጥብ 75 ሜትሪክ ቶን የጥራጥሬ ሰብል
- በአቃቂ ቃሊቲ 3 ሺሕ 325 ነጥብ 95 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል እንዲሁም 2 ሺሕ 400 ነጥብ 22 የጥራጥሬ ሰብል
- በቡራዩ ከተማ 43 ሺሕ 569 ነጥብ 25 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል እንዲሁም 116 ሺሕ 844 ነጥብ 99 ሜትሪክቶን የጥራጥሬ እህል
- በገላን 57 ሺሕ 274 ነጥብ 13 ሜትሪክ ቶን የቅባት፣ 177 ሺሕ 514 ነጥብ 82 ሜትሪክ ቶን የጥራጥሬ እህል እንዲሁም 502 ነጥብ 06 ሜትሪክቶን ሌሎች ምርቶች በድምሩ 235 ሺሕ 291 ነጥብ 2 ቶን በክምችት መገኘቱ ተገልጿል።
በሚኒስቴሩ የግብርና ምርቶች መሠረተ ልማት ቡድን መሪ ታረቀኝ ሽበሺ ወደፊት የምርቶቹ ዋጋ ይጨምራል በማለት ምርትን በወቅቱ ወደ ውጪ ገበያ ከመላክ ይልቅ በክምችት ይዞ ማቆየት የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።
110 viewsAysheshim Tiruneh Alemu, 10:15