Get Mystery Box with random crypto!

የስንዴ ዋጋ ንረት ከሰሞኑን ሕንድ በሀገሯ የምግብ አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በሚል የስንዴ | Extol ™

የስንዴ ዋጋ ንረት

ከሰሞኑን ሕንድ በሀገሯ የምግብ አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በሚል የስንዴ ምርት ከሀገር እንዳይወጣ እገዳ ጥላለች።

ነገር ግን ይሄ እገዳ በሂደት ላይ የነበሩ የስንዴ ግብይቶችን አይመለከትም።

ሕንድ የስንዴ ምርት ወደ ውጭ እንዳይላክ ማገዷን ተከትሎ ከወዲሁ የስንዴ ዋጋ በአውሮፓ ሪከርድ በሆነ ሁኔታ ጭማሪ አሳይቷል።

የስንዴ ዋጋ ወደ 435 ዩሮ (453 ዶላር) በቶን ከፍ ማለቱ ተነግሯል። ባለፈው አርብ 422 ዩሮ ነበር።

የሰሞኑን የሕንድ ውሳኔ የተለያዩ ሀገራት የኮነኑት ሲሆን ውሳኔው በዓለም የስንዴ ገበያ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ብለዋል።

ሕንድ በስንዴ ሽያጭ ላይ እገዳ መጣሏ በተለይ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የስንዴ አቅርቦት የተቋረጠባቸው የአፍሪካ እና እስያ ሀገራት ሕንድን እንደ አማራጭ ለመጠቀም አስበው ነበር።

ሕንድ በዓለም ሁለተኛዋ ከፍተኛ የስንዴ አምራች ሀገር ናት።

ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ውስጥ ከገቡበት የካቲት ወር አንስቶ በተፈጠረው ስጋት ሳቢያ የዓለም የስንዴ ዋጋ 40 በመቶው ጨምሯል።

በዓለም የስንዴ ዋጋ መናር የማዳበሪያ እጥረትም እንደምክንያት ይነሳል።

@tikvahethiopia