2022-07-07 11:08:24
#_የነብያያት_ታሪክ
#_ሙሳ_ዐለይሂ_ሰላም
እኔም ህዝቡ ለሁለት እንዳይከፈል ሰግቼ አንተ እስክትመጣ ድረስ ዝም አልኳቸው" አለው።ሙሳም ሀሩንን እዛው ትቶት ጥጃውን ወደቀረፀው ሰውዬ(ሳሚሪይ) ጋ በመሄድ፦"ምን አስበህ ነው እንዲህ ልትሰራ የቻልከው" አለው።
ሳሚሪይም፦"ያላዩትን ነገር (የጂብሪል
ባዝራ ፈረስ የረገጠችው መለምለሙን) አየሁ፤ከመልክተኛው
(ከፈረሱ ኮቴ) ዱካም ጭብጥ ዐፈርን ዘገንኩ፤(በቅርጹ ላይ)
ጣልኳትም፤እንደዚሁም ነፍሴ ሸለመችልኝ" አለው።
ጂብሪል ፊርዐውንን አሰቃይቶት ከባህሩ ውስጥ ሲወጣ የፈረሱ ኮቴ የረገጠችበትን አፈር ይህ ሰው ዘግኖ ይዞ ነበር። ከዚያም ሙሳ ጌታውን ሊገናኝ ሲሄድ ይህ ሳሚሪይ(ሳምራዊ) ከግብፅ የዘረፉትን ጌጣጌጥ አቀለጠ'ና የጥጃ ቅርፅ ሰረበት።
ከዚያም የጂብሪል ፈረስ ከረገጠችበት ቦታ የዘገነውን አፈር ደፋበት።ያን ግዜ ከወርቅ የሰራት የጥጃ ቅርፅ እንደ ጥጃ መጮህ ጀመረች። በመጨረሻም፦"ይህ እኮ ጌታችሁ ነው ሙሳ ረስቶት ሄዶ ነው" አላቸው'ና ኢስራኢላውያን ጥጃዋን ለ40 ቀናት ተገዟት። ሙሳም ለሳሚሪይ፦"ኺድ ላንተም በሕይወትህ
(ለአየኸው ሰው ሁሉ) መነካካት የለም ማለት አለህ፤ለአንተም
ፈጽሞ የማትጥሰው (አላህ የማይጥሰው የማይቀር) ቀጠሮ
አለህ፤ወደዚያም በርሱ ላይ ተገዢው ኾነህ ወደ ቆየህበት
አምላክህ ተመልከት" ብሎ ረገመው።
ኢስራኢላውያን በፈፀሙት ወንጀል የተነሳ በኪታቡ ተወርዶላቸው ከነበረውም አንድ ሰባተኛውን ከመፅሀፉ ተሰረዘ።
ኢስራኢላውያን ምንም ያህል ቢፀፀቱም አላህ ፀፀታቸውን መቀበል እንቢ በማለት ጥጃዋን ያመለኩትን ወገኖች እርስ በርስ እንዲገዳደሉ አዘዛቸው።በዚያ መሀልም የሞተው ሸሂድ እንደሚሆንም ነገራቸው።
ጥጃዋን በማምለካቸው የተፀፀቱትም ኢስራኢላውያን ለጥፋታቸው ማካካሻ እርስ በርስ መጨፋጨፍ ጀመሩ።በዚያ መሀልም በሽወች የሚቆጠሩ ኢስራኢላውያን ሞቱ። ይሄን ሲመለከቱም ሙሳ እና ሀሩን አላህን አጥብቀው መማፀን ጀመሩ።
አላህም ይቅርታውን አውርዶላቸው ግድያውን አስቆመላቸው።
ከዚያም ኢስራኢላውያን፦"ሙሳ የአላህን ድምፅ አሰማን" እያሉ ማስቸገር ሲጀምሩ ሙሳም ከኢስራኢላውያን የተወሰኑ እሙን ሰዎችን መርጦ እንዲፆሙ ካዘዛቸው በኋላ እዛ ጡር ተራራ ላይ ይዟቸው ወጣ።እነሱም፦"በል አሁኑኑ የአላህን ድምፅ አሰማን" አሉት።
ሙሳም እሽ ብሎ ወደ ተራራው ጫፍ ይዟቸው ወጣ'ና ልክ ተራራዋን ሲደርሱ የሆነ ዳመና ነገር መጣ እዚያ ዳመና ውስጥ ሙሳም ገብቶ ኑ አላቸው'ና አስገባቸው። በውስጡም ሲገቡ እርስ በርስ መተያየት እንኳን ተሳናቸው።
ዳመናውም ውስጥ እንደ ገቡ ሱጁድ አድርገው ሳለ ሙሳ እና አላህ ሲነጋገሩ ሰሙ።ሙሳም ከጌታው ጋር ያለውን ንግግር ከጨረሰ በኋላ ዳመናው ተገፈፈ። ያን ግዜ፦"በል ድምፁን ሰምተናል። እንድናምንህ ከፈለግክ እራሱን አሳየን" አሉት።
እንዲህ ሲሉ መቅሰፍት ወረደባቸው'ና ሁሉም በቅፅበት ሞቱ።
ሙሳም በጣም ተጨነቀ....እጁን ዘርግቶም፦"ጌታዬ ሆይ! ከህዝቤ መሀከል የተከበሩትን ነው መርጬ የመጣሁት፤ አሁን ሞቱ ብል ማንም እኔን አያምነኝም። ስለዚህ እባክህ አስነሳቸው" በማለት አላህን ሲማፀን ሰዎቹ ሩሆቻቸው ተመለሱላቸው።
ብድግ ብለውም፦" ሙሳ ሆይ! አንተ አላህን ጠይቀህ ምንም አይከለክልህም። ስለዚህ እባክህ እስቲ ሁላችንንም አላህ ነቢይ እንዲያደርገን ዱዓ አድርግልን" አሉት።
ሙሳም ዱዓ ሲያደርግ አብረውት የነበሩት ባጠቃላይ አንቢያእ ሆኑ።
ከዚያም ሙሳ ከጡር ተራራ ላይ ተውራትን(መፅሀፉን) ይዞ ወደ ኢስራኢላውያን በመመለስ ስለመፅሀፉ ማስተማር ሲጀምር፦"ይህ መፅሀፍ የሚለው ነገር ሁሉ ይከብዳል በዛ ላይ ሁሉንም ነገር ሀራም ይላል።አንቀበልህም" አሉት።
የኢስራኢላውያንን ጥመት አላህ ሲመለከት ጂብሪልን አዘዘው'ና በአቅራቢያቸው የሚገኘውን ትልቅ ተራራ ከስሩ ነቅሎ ወደ ሰማይ ከፍ በማድረግ ኢስራኢላውያን ላይ አንጠለጠለባቸው። ልክ ተራራው በላያቸው የሚወድቅ ይመስላል።
ከበስተኋላቸው ደሞ አስፈሪ የባህር ማዕበል መጣ።ከበስተፊታቸውም ደግሞ ነበልባል እሳት መጥቶ ድቅን አለባቸው።
ይህን ግዜ ሙሳ፦"የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ይህ ያመጣሁላችሁን ተውራት(መፅሀፍ) የማትቀበሉ ከሆናችሁ ከላያችሁ በኩል ያለውን ተራራ አላህ ይጥልባችኋል፣ከበስተፊታችሁ ባለውም እሳት ያቃጥላችኋል፣ከበስተኋላችሁም ያለው ማዕበል ያጥለቀልቃችኋል" በማለት አስገደዳቸው።
እነሱም ይህን ጉድ ሲመለከቱ፤መሸሻም እንደሌላቸው በተረዱ ግዜ ለግዳቸው የተወረደላቸውን መፅሀፍ መርሀባ ብለው ተቀበሉ።
በዛን ጊዜ ኢስራኢላውያኑ መፅሀፉን ሲቀበሉ ሱጅድ አድርጉ ተብለው ሱጁድ ሲያደርጉ በግማሽ ግንባራቸው ተደፍተው በቆረጣ አይናቸውን እያንቀዋለሉ ተራራው እንዳወድቅባቸው ይጠባበቁ ነበር።በዚሁ አጋጣሚ የነሱ የሱጁድ ሱና በግማሽ ግንባር ሆኖ ቀረ።)
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከእለታት አንድ ቀን አንድ ልጅ የአጎቱን ንብረት ለመውረስ ፈልጎ አጎቱን ገድሎ ጣለው።ከዚያም ልጁ እራሱ ወደ ሙሳ በመሄድ፦"የአጎቴ ገዳይ ኤኬሌ ነው'ና ፍረደን" ብሎ ከሰሰ።ያ ገዳይ ተብሎ የተከሰሰውም እንዳልገደለው ተከራከረ።
ሙሳም አላህ እንዲፈርድ ተማፅኖት አላህም እስራኢላውያንን አንዲትን ላም እንዲያርዱ አዘዛቸው።
ሙሳ አላህ ያዘዛቸውን ለህዝባቸው ሲነግሩ ማላገጥ ጀመሩ፦"አንተ ሰው ሞቶብናል ፍረደን ብንልህ ላም እረዱ ብለህ ታሾፋለህ እንዴ!" በማለት።
ከዚያም በድርቅና፦"ምን አይነት ላም ናት" አሉ።
ሙሳም፦"እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች ጊደር ናት ብሏል አላህ" አላቸው።
እነሱም፦"ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ መልኳ ምን እንደኾነ ለኛ ይግለጽልን" አሉት።
ሙሳም፦"እርሷ መልኳ ደማቅ ተመልካቾችን የምታስደስት ዳለቻ ላም ናት። ይላችኋል አላህ" አላቸው።
እነሱም፦"ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች ይግለጽልን፤ ከብቶች በኛ ላይ ተመሳሰሉብን፡፡ እኛም አላህ የሻ እንደኾነ በእርግጥ ተመሪዎች ነን" አሉ።
ሙሳም፦"እርሷ ያልተገራች ምድርን (በማረስ) የማታስነሳ እርሻንም የማታጠጣ (ከነውር) የተጠበቀች ልዩ ምልክት የሌለባት ናት። በማለት አላህ ይላችኋል" አላቸው።
ይህን ግዜ እንደዚህች አይነት ጊደር ፍለጋ ወጡ። ብዙ ካፈላለጉ በኋላ ይህችን ጊደር ራሷን አንድ በእናቱ መልካም የሚውል ልጅ ዘንድ አገኟት። ሊገዙት ሲሉ፦"አልሸጥም" አለ።
ብዙ ከተደራደሩ በኋለ በጊደሯ ቆዳ ሙሉ ወርቅ እንሰጥሀለን ብለው በዚህ ተስማምተው አረዷት።ካረዷትም በኋላ በጊደሯ ምላስ የሞተውን ሰውዬ እንዲመቱት ሙሳ አዘዛቸው።
ሬሳውን በጊደሯ ምላስ እንደመቱትም ሬሳው ተነስቶ፦"የወንድሜ ልጅ ውርስ ፈልጎ ነው የገደለኝ" ብሎ ተናግሮ ተመልሶ በድን ሆነ።
ከዚያም በሌላ ቀን ደግሞ ሙሳ ለኢስራኢላውያን ቆሞ ዳዕዋ እያደረገላቸው ሳለ፦"ሙሳ ሆይ! ከሰዎች ሁሉ አዋቂ ማን ነው" አሉት።
ሙሳም፦" እኔ ነኛ" ብሎ ሲመልስላቸው አላህም ሙሳን ወቀሰው'ና፦"ሙሳ ሆይ! ለኔ በሁለት ባህሮች መገናኛ ላይ አንድ ባሪያ አለኝ፤እሱም ካንተ በላይ አዋቂ ነው" አለው።
ሙሳም፦"ጌታዬ ያን ባሪያህን እንዴት ላገኘው እችላለሁ" አለው።
http://t.me/guzo5
863 views08:08