Get Mystery Box with random crypto!

EBS TV

የቴሌግራም ቻናል አርማ etv_newss — EBS TV E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etv_newss — EBS TV
የሰርጥ አድራሻ: @etv_newss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.18K
የሰርጥ መግለጫ

worldwide news🌍

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-30 20:50:29
" ገንዘብ ያለወጠው ህሊና "

በስህተት ወደ ሌላ ሂሳብ የገባ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ለባለቤቱ መመልሲን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገለፀ።

አቶ ሲሳይ ተስፋዬ በስልካቸው አንድ መልእክት ይደርሳቸዋል፡፡ በወቅቱ ሀሰተኛ መልእክት ስለመሰላቸው ብዙም ትኩረት አልሰጡትም፡፡

በጡረታ ላይ የሚገኙት አቶ ሲሳይ ዘመድም ወዳጅም ይህን ያደርጋል ብለው የሚጠብቁት ነገር ስላልሆነ በሂሳባቸው ብር 501,840.00 መግባቱን የሚናገረውን መልእክት ሀሰተኛ ነው ብለው አምነዋል፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ ሂሳባቸውን በኤ.ቲ.ኤም ሲያዩ ግን እውነትም ብር 501,840.00 ወደ ሂሳባቸው ገብቷል፡፡

አቶ ሲሳይ በጡረታ ዘመኔ ያገኘሁት ሲሳይ ነው ብለው አልተደሰቱም፡፡ ይልቁንስ በስህተት የገባ ገንዘብ መሆኑ ስለገባቸው የገንዘቡን ባለቤት ማፈላለግ ጀመሩ እንጂ፡፡

ወደ ባንክ በመሄድ የሂሳብ ዝርዝር አስወጥተው ገንዘቡን ወደ ሂሳባቸው ያስገባውን ሰው ስም አገኙ፣ የውጭ ሀገር ዜጋ  ነው፡፡

ስልኩን ከባንኩ ተቀብለው ደወሉለት፡፡ እውነትም በስህተት የገባ ገንዘብ መሆኑን አረጋገጡ፡፡ አስፈላጊውን ማጣራት አድርገው የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት መሆኑን ሲያረጋግጡም ገንዘቡን በታማኝነት መለሱ፡፡

ገንዘቡ ህይወታቸውን ሊለውጥ ቢችልም ህሊናቸውን ግን ሊለውጥ እንደማይችል የተናገሩት አቶ ሲሳይ፣ ገንዘቡን ሲመልሱ የተሰማቸው ደስታ ወደር የለውም፡፡

የሰው ገንዘብ በፍፁም እንደማይፈልጉ እምነታቸው አድርገው የኖሩት አቶ ሲሳይ፣ አጋጣሚው የሚሉትን በተግባር ሆነው ያገኙበት ሆኖ ማለፉን ተናግረዋል፡፡

ገንዘቡ በስህተት ገቢ የተደረገበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን ቅርንጫፍ ለአቶ ሲሳይ ተስፋዬ ታማኝነት እና አራያነት ያለው ተግባር የምስጋናና የአድናቆት ደብዳቤ ሰጥቷቸዋል፡፡

#CBE

@tikvahethiopia
74 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:50:29
" በ2 ጎን ፅንፍ ተይዞ እየተደረገ ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ጦርነት በጣም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው " - የቆቦ ነዋሪ

በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ያሉ ያልተረጋገጡ መረጃዎችና ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎች መሬት ላይ ያለውን እና ቀጥተኛ የጦርነት ገፈጥ ቀማሽ የሆነውን ማህበረሰብ እየጎዳ ነው።

አንድ ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡ ከቆቦ ደሴ ተፈናቅለው የገቡ የቆቦ ነዋሪ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚሰራጨው መረጃ መሬት ላይ ካለው ሀቅ እንደማይገናኝ ገልፀዋል።

" በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚታየው የፉክክር ጉዳይ ነው የሚመስለው " ያሉ ሲሆን ለአብነት ቆቦ ተለቀቀች ተብሎ የሚሰራጨው ሀሰት እንደሆነና የህወሓት ታጣቂዎች በከተማው እንዳሉ ይህን እዛው ካሉ ቤተሰቦቻቸው እንደተገለፀላቸው አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት ወቅትም የፉክክር እና የውድድር ነገር ነው ያለው በሰው ሀብት፣ በሰው ነፍስ፣ በሰው ንብረት ጨዋታ የተያዘ ነው የሚመስለው ሲሉ የማህበራዊ ሚዲያውን ሁኔታ ገልፀዋል።

እኚሁ የቆቦ ነዋሪ በ2 ጎን ፅንፍ ተይዞ እየተደረገ ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ጦርነት በጣም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው ፤ ለአብነት ቆቦ በመንግስት ኃይል ስር ገብታለች ተብሎ ከተነገረበት ሰዓት ጀምሮ ብዙ ተፈናቃይ ወገኖች እንመለስ የሚል የእግር ጉዞ ጀምሮ ነበር ብለዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ ትክክለኛ መረጃ እንዳይገኝ እና ህዝቡ እራሱን እንዳያደራጅ እያደረገው ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል ፤ " ያልተያዘውን ተይዟል፤ በዚህ ገቡ፣ በዚህ ወጡ " በሚል ህዝብ ተሸብሮ ንብረቱን ጥሎ እንዲፈናቀል ፣ ከተሞች እንዳይረጋጉ የሚያደርጉ አካላትም ቀጥተኛ የጦርነት ገፈጥ ቀማሽ ወገኖችን እየጎዱ በመሆናቸው ከድርጊታቸው ቢታቀቡ ሲሉ አንድ የቤተሰባችን አባል መልዕክታቸውን ልከዋል።

@tikvahethiopia
70 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:50:29
" ይህ ቀን ያልፋል ፤ ብንተሳሰብስ ? "

በዚህ በችግር ወቅት የተገኙበትን ማህበረስብ ከማገዝ ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያሯሩጡ አንዳንድ አካላት እጅግ በጣም አሳፋሪ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ባገረሸው ግጭት ሳቢያ በርካታ ሰዎች በተለይም ሴቶች እና እናቶች እንዲሁም አዛውንቶች ግጭት ያለባቸውን አካባቢዎች በመልቀቅ ሰላም እና ደህንነት ፍለጋ ለመሄድ እየተገደዱ ነው።

በአሁን ሰዓት ዳግም የጦርነት ቀጠና በሆኑት የአማራ ክልል አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች ያለፈው ቁስላቸው፣ ህመማቸው ሳይሽር ዳግም ለከፍተኛ ለስቃይ ተዳርገዋል።

ህዝቡ ምን ያህል ችግር ላይ እና ሰቆቃ ላይ እንዳለ እየታወቀ ግን አንዳንድ ግለሰቦች የራሳቸውን ወገኖች በተሽከርካሪያቸው ከቦታ ወደ ቦታ ለመውሰድ እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ እየተቀበሉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ያላቸው ገንዘቡን ይሰጣሉ የሌላቸው ግን በእግር ከከፍተኛ ድካም ጋር ሰላምን ፍለጋ ለመሄድ እየተገደዱ ነው።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት በትንሽ ኪሎ ሜትር እስከ 500 ብር ድረስ እና ከዛም በላይ እንደሚቀበሉ ለመስማት የቻልን ሲሆን በዚህ በችግር ወቅት እንዲህ የሚያደርጉ አካላት ቁጥጥር ሊደረግባቸው ከምንም በላይ ደግሞ ትልቁ ፈረጅ ህሊና ነውና ለህዝባቸው ቢያስቡ መልካም ነው።

ይህ ቀን ያልፋል ፤ የዛሬው ጭንቀት እና መከራ ወቅት ይቀየራል ፤ በዚህ ልክ መጨካከንና ህገወጥ ስራ መስራት አይገባም።

አሁን ላይ በመንግስት ቁጥጥር ስር ባሉት እና ግጭት ባለበት መስርመር ያሉ ከተሞች ገና ለገና ተፈናቃዮች መጡ በሚል ልክ እንዳለፈው ጊዜ ዋጋ ለመጨመር የሚሯሯጡ ነጋዴዎችም በመኖራቸው የሚመለከተው አካል ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ ይገባል።

@tikvahethiopia
69 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:50:29
#ATTENTION

ዳባት !

የዳባት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ም/ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ምክር ቤቱ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል ፦

- በከተማዉ ውስጥ ማንኛዉም ሰዉ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኃላ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ውሳኔ ተላልፋል።

- ማንኛዉም መጠጥ ቤቶችና ምግብ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 በኃላ አገልግሎት እንዳይሰጡ ተከልክለዋል።

- በከተማው ማንኛውም ተሽከርካሪ ባጃጅን ጨምሮ ከምሽቱ 12:00 በኋላ እና ጧት ከ12:00 ስዓት በፊት ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ተክልክሏል።

- በከተማው የሚገኙ አልጋ ቤቶች ፣ቤት አከራዮች እና ሆቴሎች ማንነቱ ያልታወቀን ሰው ማንነቱን በመለየት በመረጃ ፎርም ሞልተው ማከራየት እና አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ለህግ አካላት እንዲያሳውቁ ተብለዋል።

- የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከዳባት ዳራ እና ከዳባት ወቅን ብቻ እንዲያሽከረክሩ የተወሰነ ሲሆን ከዳባት ወደ አጅሬ መስመርና ከዳራ ገደብየ ማሽከርከር ተከልክሏል።

- የዳባት ከተማ ፈቃድ የሌለዉ ባጃጅ ከዳባት ወደ ሌላና ከሌላ ቦታ ወደ ዳባት ማሽከርከር ተከልክሏል።

- ለፀጥታ ስራ ከተሰማሩት ዉጭ ማንኛዉም ግለሰብ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

ከዚህም በተጨማሪ የፀጥታ ም/ቤቱ ፤ ማንኛውም ሰው የህዝብን ስነልቦና የሚጎዳ ማንኛውም ሀሰተኛ ወሬ ሆነ አሉባልታ ከማሰራጨት እንዲቆጠብ እና መላው የከተማው ማህበረሰብ በአደረጃጀቶቹ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል በከተማው ተከራይተዉ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች ወደ ካፕ የሚመለሱበት ምቹ ሁኔታ እንዲመቻች ከሚመለከታቸዉ አካለት ጋር ስራ እየተሰራ መሆኑ ምክር ቤቱ ገልጿል።

@tikvahethiopia
118 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:50:22
#Update

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ባደረባቸው በስጋት ምክንያት ግቢያቸውን ለቀው የወጡ ተማሪዎችን በሚመለከት ውሳኔ አሳለፈ።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በ22/12/2014 ዓ.ም ባደረባቸው ስጋት ምክንያት የተነሳ ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል።

በዚህ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

1ኛ. የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ #በቀጣይ_ዓመት ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ ይሆናል።

2ኛ. የክረምት መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ የተጀመረውን ትምህርትና ፈተና ለማጠናቀቅ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ መስከረም 03/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
372 views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:50:21
#ሳፋሪኮም

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በድሬዳዋ ከተማ ጀምሯል።

ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት ነው።

በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን ደንበኞች በዐ7 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት ይችላሉ፡፡

ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል ያገኛሉ።

የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎት መጠቀም መቀጠል ይችላሉ፡፡

በከዚራ፣ መስቀለኛ እና ኮርኔል ያሉ ሦስት የሳፋሪኮም ሽያጭ ማዕከሎች ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ለመስጠት ክፍት እንደሆኑ ተገልጿል።

በድሬዳዋ ከተማ አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ ይችላሉ፡፡

@tikvahethiopia
354 views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:14:37
#ATTENTION

ደሴ !

ከደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የከተማው ሰላም እና ደህንነት ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ፦

- የምግብ ቤቶች ፣ የምሽት መጠጥ ቤቶች/ግሮሰሪዎች/ ከምሽቱ 1፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በማንኛውም ምክንያት አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ ተከልክሏል።

- ማንኛውም ምርት ላይ የዋጋ ጭማሬ የሚያደርጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል።

- በመፈናቀል ሆነ በሌላ ማንኛውም ምክንያት ወደ ደሴ ከተማ የገቡ ተፈናቃዮች የከተማውን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል የፀጥታ ኃይሎች ለጋራ ደህንነት ለሚተገብሯቸው የፍተሻና የቅድመ-ጥንቃቄ ስራዎች ተባባሪ የመሆን ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

- አልጋ ቤት፣ የመኖሪያ ቤት ወይም መደብ ቤት አከራዮች የየትኛውንም ተከራይ ማንነትን የሚገልፅ መረጃ ለፀጥታ ተቋማት የመስጠት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

- ወደ ደሴ በማንኛውም ምክንያት የገቡ እንግዶች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- ከተፈቀደላቸው የከተማው የፀጥታ ሃይሎች ውጭ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ ተከልክሏል።

- ከዛሬ ጀምሮ የትኛውም የከተማችን ነዋሪ ከምሽቱ 2:00 /ሁለት/ ሰዓት ጀምሮ በተናጠልም ሆነ በጋራ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- በከተማ ደረጃ እውቅና ያላቸው የተሰጣቸው የታክሲ አሽከርካሪዎች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ብቻ ህዝቡን እንዲያገለግሉ ተወስኗል።

- በሁሉም አካባቢወች የሚገኙ ባጃጆች እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ውሳኔ ተላልፏል።

- የDSTV አገልግሎት መስጫዎች ፣ በጋራ ተሰብሰቦ ጫት የሚቃምባቸው መቃሚያ ቤቶች ፣ የሽሻ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ በይፋም ሆነ በስውር አገልግሎት መስጠት ተከልክሏል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
482 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:14:37
#ATTENTION

ወልድያ !

የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን አካባቢ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ አስቀምጧል።

በዚህም ፦

• ከተመደበው የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ሰው መንቀሳቀስ #ተከልክሏል።

• ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጠው ተሽከርካሪ ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ እንደማይችል ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tikvahethiopia
369 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 13:14:01
ጉዳፍ ፀጋይ አንደኛ ሆና አጠናቃለች።

በሶስተኛው ምድብ የማጣሪያ ውድድር ፤ ጉዳፍ ፀጋይ አንደኛ ደረጃ ይዛ በበላይነት አጠናቃለች።

ወደ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር አልፋለች።

በ1,500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር ሁሉም ሴት አትሌቶቻችን ፦

ጉዳፍ ፀጋይ
ፍሬወይኒ ኃይሉ
ሂሩት መሸሻ በድንቅ ብቃት ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፈዋል።

ነገ ለሊት 11:05 ላይ #የግማሽ_ፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል።

እንኳን ደስ አለን !

ቲክቫህ ስፖርት : https://t.me/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia @tikvahethsport
335 views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 13:14:01
ፍሬወይኒ ኃይሉ ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።

በሁለተኛው ምድብ የማጣሪያ ውድድር ፤ ፍሬወይኒ ኃይሉ ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። ወደ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር አልፋለች።

እንኳን ደስ አለን !

ቲክቫህ ስፖርት : https://t.me/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia @tikvahethsport
277 views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ