Get Mystery Box with random crypto!

የጃራ ተፈናቃዮች ጉዳይ! የጃራ ተፈናቃዮች ትናንት ወደ አፋር ጭፍራ ቢሄዱም አትገቡም ተብለው ዛሬ | EBS TV

የጃራ ተፈናቃዮች ጉዳይ!

የጃራ ተፈናቃዮች ትናንት ወደ አፋር ጭፍራ ቢሄዱም አትገቡም ተብለው ዛሬ ወደነበሩበት መመለሳቸውን ተናግረዋል።

በጃራ በመጠለያ ጣቢያ የሴቶችና ህፃናት አስተባባሪ ወ/ሮ ዘነበወርቅ ጣውዬ ፥

" በካምፑ ውስጥ ከተለያዩ የራያ፣ ኮረም ቆቦና ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያው የነበሩ ከ30 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ሰሞኑን ባገረሸው ግጭት በስጋት ሳቢያ ወደ ጭፍራ ተጉዘው አዳራቸውን በዚያው አድርገዋል።

ተፈናቃዮቹ ከማንነት ጋር በተያያዘ ከ 'ህወሓት' ጥቃት ይደርስብናል በሚልና ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የውሃና የምግብ እጥረት በመከሰቱ ጭምር የሸሹ ናቸው። "

ከተፈናቃዮች መካከል አቶ ዝናቡ መሰለ ፦

" ሁሉም ተፈናቃይ ለሶስት ቀናት በመጠለያ ጣቢየው ቢቆይም፣ የምግብና የውሀ እጥረት በመከሰቱ እንደገና ለመፈናቀል ተገደናል።

የአማራ ክልልን አቋርጠን አፋር ክልል ብንደርስም ጠብቁ ተብለን እዛው ሜዳ ላይ አድረን ወደመጣቹበት ተመለሱ ተለናል።

በዚህም ምክንያት ዛሬ እየተመለስን ቢሆንም ብዙዎች አቅመደካሞች ህፃናትና እናቶች በየበረሀው ቀርተዋል።

አካባቢው እጅግ ሙቀት በመሆኑ ህፃናትና የሚያጠቡ እናቶች ለከፍተኛ የውሀ ጥምና ርሀብ ተጋልጠዋል። "

ትናንት ከጃራ ጭፍራ ዛሬ እንደገና ከጭፍራ ጃራ ተጉዘው ወደ መጠለያ ጣቢያው ከደረሱት መካከል አንዳንዶቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ቁሳቁሶችና የማብሰያ እቃዎች በመዘረፋቸው፣ የውሀና የምግብ አቅርቦት ባለመኖሩ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ገልፀዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዓለሙ ይመር ፦

" መጠለያ ጣቢያውን ሁሉም ተፈናቃዮች አለቀቁም። የሄዱትም ቢሆኑ እተመለሱ ነው ብለዋል፡፡  የእርዳታ እህልና ቁሳቁስ በተመለከተ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ቦታው ይላካል " #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia