Get Mystery Box with random crypto!

#OFC የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ በላከው መግለጫ ' በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በተቀሰቀሰው ጦርነ | EBS TV

#OFC

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ በላከው መግለጫ " በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በተቀሰቀሰው ጦርነት እና በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት በመባባሱ እጅግ አዝናለሁ " ብሏል።

ፓርቲድ የነዚህ ግጭቶች መባባስ እና መቀጠል ህዝቡን ዳግም ለከፋ ሞት እና መፈናቀል የሚዳርግ ከመሆኑ ባሻገር ለንብረትና መሰረተ ልማቶች ውድመት የተዳረጉ አካባቢዎችን ለበለጠ አለመረጋጋት ይዳርጋል ብሏል።

ኦፌኮ ጦርነቶቹ ከመቀሰቀሳቸው ቀድም ብሎ ጦርነት ለኢትዮጵያ ውስብስብ የፖለቲካ ችግሮች መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል እንደገለፅኩት አሁን ዳግም በአፅንዖት እገልፃለሁ ብሏል።

አሁን ያሉት ችግሮች በዘላቂነት ሊፈቱ የሚችሉት በእውነተኛ እና ሁሉን አቀፍ ድርድር ብቻ ነው ሲል እምነቱን ገልጿል።

በሁሉም ወገን ያሉ ተፋላሚ ሀይሎች ግጭቱን በማብረድ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲሹ ጠይቋል።

ዓለም አቅፊ ማህበረሰብ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ሁሉ ተጨማሪ ሞት እና የዜጎችን መከራ ለማሰቀረት በንቃት እና በተቀናጀ መልኩ ይረባረብ ሲልም ጥሪ አሰምቷል።

ኦፌኮ በኦሮሚያ እየተስፋፋ ነው ያለውን ግጭት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለመፍታት ቀርቶ እውቅና ሊሰጠው አልቻለም ያለ ሲሆን ይህ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

በክልሉ በተለይም በግጭትና በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲልም ገልጿል።

የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እየተባባሰ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በድርድር እንዲፈታ ሁኔታዎችንን እንዲያመቻች ጠይቋል።

ፓርቲው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ገዥው ፓርቲ፣  ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሚዲያ ተቋማት፣ የማህበራዊ ሚዲያ ባለሙያዎች እና አክቲቪስቶች ግጭቱን ከሚያባብሱ ንግግሮች እንዲታቀቡ እና ችግሩን ለማርገብና ለመፍታት በአንድ ድምፅ እንዲተባበሩ ተማጽኗል።

@tikvahethiopia