#UnitedNation
የተመድ ዋና ፀሀፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትላንት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው የነበረ ሲሆን በመግለጫው ላይ የሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይን አንስተው ነበር።
ስቴፋን ዱጃሪች ምን አሉ ?
- በሰሜን ኢትዮጵያ አሁንም ግጭት መቀጠሉን እና አሁን ላይ ያለድ ሁኔታ ውጥረት የተሞላበት እንደሆነ ገልፀዋል።
- የአፋር ክልል ከትግራይ ጋር በሚዋሰንባቸው ቦታዎች ማለትም በያሎ እና ጉሊና ወረዳዎች እየተካሄደ ባለ ውጊያ ሳቢያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል።
- በአፋር እና አማራ አዋሳኝ ቦታ ጭፈራ ወረዳ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሚገልፅ ሪፖርት መኖሩን አመልክተዋል።
- በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከሚገኘው የጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ተጠልለው የነበሩ 30 ሺህ ሰዎችም ለሁለተኛ ጊዜ ተፈናቅለዋል።
- ዳግም ባገረሸው ግጭት ሰዎች እየተፈናቀሉ መሆኑ የሰብዓዊ መብት ፍላጎትን ይጨምራል ብለዋል።
(ተጨማሪ ከላይ ተይይዟል)
@tikvahethiopia