Get Mystery Box with random crypto!

etv ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ etv_57 — etv ዜና E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etv_57 — etv ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @etv_57
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.46K
የሰርጥ መግለጫ

የETV ምርጥ ምርጥ ዜናዎችን በቅርብ ለማግኘት ይቀላቀሉ .... የETV OFFICIAL ቻናል እንዳልሆነ ይታወቅልን፡፡.... ግን ከዋናው ምንጭ ይቀዳል፡፡
ሀሳብ ለመለዋወጥ @ETV57_bot ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን።
ቅሬታ ካለዎት ቻናላችንን ከመልቀቅዎ በፊት @ETV57_bot ላይ ይላኩልን።
@ETV_57 @ETV_57

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-02-11 14:40:54 በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚወስዱ ተገለፀ !

የትምህርት ሚኒስቴር የ 2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተናን በተመለከተ በዛሬው እለት መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒኤችዲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ12ሺ ህ በላይ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በአካባቢው የትምህርት መሰረተ-ልማቶች ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ፈተናቸውን በአካባቢያቸው በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተፈታኞች በአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ትምህርት ቢሮዎች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታትም ተፈታኞችን በክልሉ ወደሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማጓጓዝ ስራዎች እንደሚሰሩ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ተፈታኞቹ ፈተናቸውን የሚወስዱባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም መቐለ ፣ አክሱም ፣ አዲግራት እንዲሁም ራያ የኒቨርስቲዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
#share
@ETV_57
15.4K views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-11 12:54:40 የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀት ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር በኦንላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ዛሬ አስታውቋል።

#በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮቪድ-19 ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ነው በወረቀት ለመስጠት የታሰበው ብሏል ሚኒስቴሩ።

ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ፈተናው እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል።
#tikvah

#Share
@Ethio_Matric
9.7K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ