Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚወስዱ ተ | etv ዜና

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚወስዱ ተገለፀ !

የትምህርት ሚኒስቴር የ 2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተናን በተመለከተ በዛሬው እለት መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒኤችዲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ12ሺ ህ በላይ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በአካባቢው የትምህርት መሰረተ-ልማቶች ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ፈተናቸውን በአካባቢያቸው በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተፈታኞች በአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ትምህርት ቢሮዎች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታትም ተፈታኞችን በክልሉ ወደሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማጓጓዝ ስራዎች እንደሚሰሩ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ተፈታኞቹ ፈተናቸውን የሚወስዱባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም መቐለ ፣ አክሱም ፣ አዲግራት እንዲሁም ራያ የኒቨርስቲዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
#share
@ETV_57