Get Mystery Box with random crypto!

ሰ/መ/ቁጥር 222681 ጥቅምት 04 ቀን 2015 ዓ/ም የቤት ሽያጭ ውሉ በውል አዋዋይ ፊት ያልተ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ሰ/መ/ቁጥር 222681 ጥቅምት 04 ቀን 2015 ዓ/ም

የቤት ሽያጭ ውሉ በውል አዋዋይ ፊት ያልተደረገ ከሆነ በውሉ ላይ የሰፈሩት ማናቸውም የውል ቃሎች ፊርማን ጨምሮ ያለቅድመ ሁኔታ በሰነዱ ላይ በሰፈሩበት አግባብ የሚታመኑ ሳይሆኑ በሌላ አግባብነት ባለው ማንኛውም ማስረጃ ሊስተባበሉ የሚችሉ ናቸው፡፡
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ስር በጽሑፍ ሰነድ ላይ የሚገኝ የስምምነት ቃል እንዲሁም በላዩ ላይ የተጻፈው ቀን በፈራሚዎቹ መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነው የሚለው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1678/ሐ፣1719/2 እና 1723/1 ስር በተደነገገው መሰረት በሕግ የታዘዘውን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ ለተደረገ ውል እንጂ ለማንኛውም ውል አይደለም፡፡
@habeshaadvocatesLLp

t.me/ethiolawtips