Get Mystery Box with random crypto!

ሰ/መ/ቁ 35962 (ያልታተመ) ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፊት ያልተደረገ የቤት ሽያጭ ውል | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ሰ/መ/ቁ 35962 (ያልታተመ)
ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፊት ያልተደረገ የቤት ሽያጭ ውል መሰረት በማድረግ ገዢ ቤቱን የሚመለከቱ ማንኛውም ሰነዶች እንዲያስረክበው በሻጭ ላይ ክስ አቅርቦ ጉዳዩን የሚያየው ፍርድ ቤት የቤት ሺያጭ ውሉ በፍ/ሕ/ቁ. 1723 መሰረት በዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ፊት ባለመደረጉ የህግ ውጤት የለውም የሚል ድምዳሜ ላይ ከደረሰ ሻጭ ሰነዶችን ለማስረከብ እንደማይገደድ ከመወሰን አልፎ የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ ውሳኔ ሊሰጥ አይገባም። ምክንያቱም የቤት ሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ የቀረበ የዳኝነት ጥያቄ ባለመኖሩ ፍ/ቤቱ በዝርዝር ባልቀረበ ወይም በግልጽ ባልተጠየቀ ጉዳይ ላይ ውሣኔ መስጠቱ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 282/2/ የሚቃረን ነው።
habeshaadvocatellp
t.me/ethiolawtips