#WolaytaSodoUniversity #የጥሪ_ማስታወቂያ ሪማስታወቂያ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለ 1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ!! በትምህርት ሚኒስቴር በተደረገ ድልድል መሠረት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ የ 1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ የቅበላ ጊዜ ከሚያዚያ 27 እስከ 28/2014 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን፦ 1ኛ. የምዝገባው ሂደት በ Online ሆኖ፤ የምዝገባ ጊዜ ከሚያዚያ 27 እስከ 28/2014 ዓ.ም፤ 2ኛ. በተቋሙ ህገ ደንብ እና ተማሪዎች መከተል ስለሚገባቸው የስነ ምግባር ደንብ ላይ ገለጻ (Orientation) ሚያዚያ 29/2014 ዓ.ም፤ 3ኛ. የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ (DOCO) ግንቦት ዐ1/2ዐ14 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ፤ የስፖርት ትጥቅ፣ አንሶላ እና የትራስ ጨርቅ ይዛችሁ እንድትመጡ ጭምር እናሳውቃለን፡፡ #ማሳሰቢያ፡-ጥሪ ከተደረገበት ጊዜ ቀድሞም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን!! ምንጭ፡ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደደር የሬጅስተራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት 1.7K viewsYaredo man, edited 18:45