HawassaUniversity በ2014 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ #በኦንላይን ከግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም በዋናው ግቢ እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ ስለምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር መረጃዎች በተቋሙ ድረ-ገጽ https://hu.edu.et እና በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ገጾች የሚገለጹ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦ • የ12ኛ እና የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው • ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ዋናውና ኮፒው • ጉርድ ፎቶግራፍ (4) • የሌሊት አልባሳት • የስፖርት ትጥቅ ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ግንቦት 10 እና 11/2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ ተብሏል፡፡ ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ፨ለጥቆማ 2.0K viewsYaredo man, 18:04