Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ዩኒቨርስቲ መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_university_info — ኢትዮ ዩኒቨርስቲ መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_university_info — ኢትዮ ዩኒቨርስቲ መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_university_info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.06K
የሰርጥ መግለጫ

🛂 ይህ ቻናል የግቢ ተማሪዎችን ችግር እግር በእግር እየተከታተለ ለሚማለከተዉ አካል ያሳዉቃል መፍትሔ እንድያገኝም ጥረት ያደርጋል።
👉ለስራችን ጥራት የእናንተ ከጎናችን መሆን ትልቅ ዋጋ አለዉ።
ይህ ቻናል
የናንተዉ
ለናንተዉ
ከናንተዉ
የሆነ ቻናል ነዉ።
👉 እባካችሁ አስተያየት/Comment ካላቹ
እዚህ ላይ ፃፉልን
@think_positiive
💙💛ከልብ እናመሰግናለን

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-04 13:04:25
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ 15 ብር የነበረውን እለታዊ የተማሪዎች ምገባ ወጪ በራሱ ፈቃድ ወደ 34 ብር አሳድጎ ተገኘ

አሶሳ ዩኒቨርስቲ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቀመጠውን እለታዊ የተማሪዎች ምገባ ዋጋ በሕግ ከተፈቀደለት ውጪ በአንድ ተማሪ ላይ በቀን 19 ብር ጨምሮ ለአንድ ተማሪ በቀን 34 ብር ተመን ሲመግብ እንደነበር በኦዲት መረጋገጡ ተሰምቷል።

ዩኒቨርሲቲው ገንዘብ ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያስቀመጠውን እለታዊ የተማሪ ምገባ ወጪ ተመን ማለትም 15 ብር የነበረውን፣ ወደ 34 ብር ከፍ በማድረግ በፈቃዱ በማኔጅመንት አጽድቆ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አረጋግጫለሁ ብሏል።

ሙሉ የአዲስ ማለዳን ዘገባ ያንብቡ
https://bit.ly/3AmW4SG
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
478 views Muhaba Mass , 10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 10:52:23
#AddisAbaba

የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ መሰጠት ጀምሯል።

ፈተናው ከዛሬ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሦሥት ቀናት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ማስታወቁ አይዘነጋም።

ከተማ ዐቀፍ ፈተናው በአዲስ አበባ በሚገኙ 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች እየተሰጠ ሲሆን 1 ሺህ 800 ፈታኞች እና 450 ሱፐር ቫይዘሮች ፈተናውን እየተቆጣጠሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በዛሬው የፈተና ውሎ ጠዋት የአማርኛ እና እንግሊዘኛ ፈተናዎች እየተሰጡ ሲሆን ከሰዓት ሂሳብ እና ባዮሎጂ ፈተናዎች ይሰጣሉ።

በአጠቃላይ በከተማዋ ከ71 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
409 views Muhaba Mass , 07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 10:52:23
#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባው ዘመናዊ የስብሰባ አዳራሽ ተመርቋል፡፡

የመሰብሰቢያ አዳራጁ በአንድ ጊዜ ከአራት ሺህ በላይ ሰዎችን ማስተናገድ ይችላል ተብሏል፡፡

ዋና የስብሰባ ማዕከሉ ዘመናዊ የድምጽ መሳሪዎች፣ የአየር ማቀዝቀዣ እና ካሜራዎች ተገጥመውለታል፡፡

የስብሰባ ማዕከሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርሲቲውን የ2014 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን ቅዳሜ ዕለት በማስመረቅ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በቀጣይ አዳራሹ ለመንግስት እና የግል ተቋማት፣ ለኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች፣ ለአውደ ርዕይ እና ሌሎች ዝግጅቶች በቅርቡ የኪራይ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከ203 ሚሊዮን ብር በላይ ለስብሰባ ማዕከሉ ግንባታ ወጪ አድርጓል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info
315 views Muhaba Mass , 07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ