Get Mystery Box with random crypto!

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ 15 ብር የነበረውን እለታዊ የተማሪዎች ምገባ ወጪ በራሱ ፈቃድ ወደ 34 ብር አሳ | ኢትዮ ዩኒቨርስቲ መረጃ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ 15 ብር የነበረውን እለታዊ የተማሪዎች ምገባ ወጪ በራሱ ፈቃድ ወደ 34 ብር አሳድጎ ተገኘ

አሶሳ ዩኒቨርስቲ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቀመጠውን እለታዊ የተማሪዎች ምገባ ዋጋ በሕግ ከተፈቀደለት ውጪ በአንድ ተማሪ ላይ በቀን 19 ብር ጨምሮ ለአንድ ተማሪ በቀን 34 ብር ተመን ሲመግብ እንደነበር በኦዲት መረጋገጡ ተሰምቷል።

ዩኒቨርሲቲው ገንዘብ ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያስቀመጠውን እለታዊ የተማሪ ምገባ ወጪ ተመን ማለትም 15 ብር የነበረውን፣ ወደ 34 ብር ከፍ በማድረግ በፈቃዱ በማኔጅመንት አጽድቆ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አረጋግጫለሁ ብሏል።

ሙሉ የአዲስ ማለዳን ዘገባ ያንብቡ
https://bit.ly/3AmW4SG
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info