Get Mystery Box with random crypto!

በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ከመጪው ዓመት ጀምሮ ተግባራ | ኢትዮ ዩኒቨርስቲ መረጃ

በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ከመጪው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ሊደረግ ነው።

እስካሁን ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የቴክኒክና ሙያ ሥርዓተ ትምህርት ጉድለቶች እንደነበሩበት በጥናት መለየቱን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ተሻለ ብሬቻ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በመሆኑም ጉድለቶቹን የሚሞላና ሰልጣኞች በሁሉም ሙያ የተሟላ እውቀትና ክህሎት ይዘው እንዲወጡ የሚያደርግ አዲስ ሥርዓት ትምህርት በመጪው ዓመት ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

ሥርዓተ ትምህርቱ የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ኢንዱስትሪዎች ተሳትፈውበት የተዘጋጀ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ለኢፕድ ተናግረዋል።

"ሥርዓተ ትምህርቱ ሠልጣኞች ኮሌጆች ውስጥ እያሉ እንዴት ሥራ መፍጠር እና ራሳቸውን ለሥራ ማዘጋጀት እንደሚችሉ በተግባር የሚለማመዱበትን ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን" ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ከ1 ሺህ 800 በላይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ይገኛሉ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info