ከ10 ሺህ በላይ የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች የምረቃ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በአዲስ አበባ በሚገኙ 14 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ትምህርታቸውን የተከታተሉ 10 ሺህ 120 የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች የምረቃ ስነ-ስርዓት በሚሌኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው። ተመራቂዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ስልጠናና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር በሚገኙ 6 የፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጆች እና 8 ኮሌጆች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሰለጠኑ ናቸው። ተመራቂዎቹ በቴክኒክና ሙያ ዘርፎች ከደረጃ 2 እስከ ደረጃ 5 የተለያዩ ስልጠናዎች መውሰዳቸው የኢፕድ ዘገባ ያመለክታል። ━━━━━━━━━━━━━━━━━ Join & |||_Support us @ethio_university_info @ethio_university_info 711 views Muhaba Mass , 13:32