Get Mystery Box with random crypto!

ethioግጥም(የእፁብ ግጥሞች)✍✍✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ et12sub — ethioግጥም(የእፁብ ግጥሞች)✍✍✍ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ et12sub — ethioግጥም(የእፁብ ግጥሞች)✍✍✍
የሰርጥ አድራሻ: @et12sub
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 292
የሰርጥ መግለጫ

ምድር ላይ የማይቻለው አለመቻል ብቻ ነው
ስለመረጣቹን ምርጫችን ናቹ
ለሀሳብ አስተያየት
@etsubaloveindia ያነጋግሩን
የእፁብ ግጥሞችናድርሰቶች
አስተማሪ ጥቅሶችከ90's ሙዚቃ ጋር
በዚ ቻናል እየተዝናኑ እውቀት ይቀስማሉ!!
@ግጥምናጥቅሶች

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-02 19:56:24 ረስተኸኛል እንዴ?

ማለት?

ማለት ስለተለያየን ከረሳኸኝ ብዬ ነው

ተለያይተናል እንዴ?

ማለት ስለተጣላን ከተለያየን ብዬ ነው


ተጣልተናል እንዴ?


ማለት ስለተኮራረፉን ከተጣላን ብዬ ነው


ተኮራርፈናል እንዴ?


አንተን ትቼ ሌላ ወንድ ጋር ስለሄድኩ ካኮረፉከኝ ብዬ ነው


ትተሽኝ ሄደሻል እንዴ?


ማለት?


ማለትማ ረስቼሻለው



እፁብ ዘመቻ

join Us
@et12sub
@et12sub
271 views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 18:26:04 እድሜሽ ና አንቺ


ድሮ ልጅ እያለን ትዝ ይልሻል አይደል፣
አንቺ ትሄጅ ነበር በናቴ ስታዘል።
ኬኩን ስንቆርሰው ሻማ ስንደረድር፣
ከኔ ይበልጥ ነበር ያንቺ ሻማ ቁጥር።
ታድያ ዛሬ ደርሶ ምን ታምር ቢመጣ??
እኔ ስሸመግል አንቺ ተባልሽ ሚጣ!


እፁብ ዘመቻ

join us
@et12sub
@et12sub
958 views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 18:23:26 Voice message

በድን ላፈቀረ

እፁብ ዘመቻ

join Us
@et12sub
@et12sub
650 views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 20:26:10 ስትናፉቀኝ ምን ላርግ?? እፁብ ዘመቻ


አንተ ስናፉቀኝ……
እንዳላንጎራጉር በትዝታ ዜማ፣
ሀላፊው አግዳሚው ይህ ጉዴን ከሰማ፣
እሬሳ ናፈቀች አበደች እያሉ፣
ከንፈር መጣጭ መስለው ልቤን ያደማሉ።


በምታምነው አምላክ፣
ስናፉቀኝ ምን ላርግ?

ላንተ እንዳልተነፉስ የናፉቆቴን ሲቃ፣
ጆሮህ ከኔ ርቋል አይሆነኝ ጠበቃ።
አይኖችህ ላያዩኝ በናፍቆት ስቀጣ፣
መናፈቄ በዛ አንተ ላትመጣ።
ልብህ እኔን ትቶ ሲገባ ካፈሩ፣
ምነው ይህ ናፍቆትህ አለመቀበሩ?

ምን ላርግ ስትናፍቀኝ?
ሰመመን ገደለኝ።

አፈርህን ምሼ ከመቃብርህ ስር፣
ጮኬ እጣራለው ትሰማ ይመስል።
የአላዘር ሞትን ቢሰጥህ ምን አለ፣
ውስጤን ባሳምነው ትንሳዬህ እንዳለ።

በምታምነው አምላክ ፣
ስትናፉቀኝ ምን ላርግ?

አንተ እያለህ የነበሩ፣
ዛሬ ባጣህ ምነው ቀሩ?
ሰሚ የለኝ ማማክረው፣
ምናፍቅህ ብቻዬን ነው።

እኔማ፦
ከሞተው ባላንስም፣
ካለው ስነፃፀር፣
ተንቀሳቃሽ እሬሳ ነኝ፣
ያንተ ናፉቆት የገደለኝ።
ምነው ሞት ሀያሉ ቦታ ቢቀይረኝ፣
እኔን ይዞ ቢሄድ አንተን ከሚነጥቀኝ።

በምታምነው አምላክ ፣
ስትናፍቀኝ ምን ላርግ?

ትትሳዬህን ብጠብቀው እንደቃሉ፣
አበድሽ አሉ ያዩኝ ሁሉ።
ቅሉ ምኔ ያደርጉት ፣
የናፍቆትን ቅጣት፣
ኬት አውቀው መች አዩት።


የናፈቁትን ሰው ማግኘት ከተቻለ ፣
አንተ ወራጅ ውሀ ብትሰጠኝ ምን አለ።
ሞትህን ባምነውም ትነሳ ይመስል፣
ጮኬ እጣራለው ከመቃብርህ ስር።


ምላርግ ስናፉቀኝ?
አንዴ ተለመነኝ?
እመጣለው በለኝ።

እግዜሩን አሎቅሰው ስራው ለበጎ ነው፣
አንተን የወሰደህ እኔን ለማኖር ነው።
የሄደን ሚያስረሳ መፉትሄማ ካለ፣
እኔም እንድረሳው ብትነግሩኝ ምን አለ።

ምን ያህል ቅጣት ነው ምንኛ መጎዳት?
በማያገኙት ሠው በናፉቆት መቀጣት።

አንዴ ተለመነኝ፣
ጆሮህን አውሰኝ፣
በምታምነው አምላክ፣
ስትናፉቀኝ ምን ላርግ??

እፁብ ዘመቻ join Us
@et12sub
261 views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 20:02:06 አንድ ቀን ያሰብነው ሁሉ ይሳካል
አንድ ቀን ያለምነው ሁሉ ይሆናል
አንድ ቀን ህልማችን እውን ይሆናል

ግን ለዚህ አንድ ቀን ብዙ ቀናቶችን በትእግስት
ማለፉ ይኖርብናል ምክንያቱም
አሁን ላይ የምንናደድባቸው ፣ተስፋ ያጣንባቸው፣ እልህ የጨረስንባቸው ፣ያነባንባቸው፣ የተሸነፋንባቸው ቀናቶች ናቸው ተደምረው ምንናፉቃትን ያቺን አንድ ቀን የሚሰጡን

ለዚም ትግስትን ከመዳፋችን አጥብቀን እንያዛት
እኛ ያቺን ቀን ማምጣት እንችላለን ምክንያቱም እኛ የተፈጠርነው ሁሉን ከሚችለው ፈጣሪ ነውና


እፁብ

join Us
@et12sub
@et12sub
938 views17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 08:32:25 የሚያግዝሽ ላይኖር፤
ያይኖችሽን እምባ ፤ ፈጥኖ የሚያብሰው
እኔን ላይል ወገን፤
ከወደቅሽ ኋላ ፤ ሁሉም የሚደርሰው

ወደ ውስጥ ላይፈስ ፤ እምባሽ ሰርስሮ አንጀት
ማቆሙን እያወቅሽ ፤ ዞሮ ማየት አንገት
ባክሽ ሳግ አይውጣሽ፤
ለማን? ማለት ልመጅ ፤ ከፍቶኝ የምደበት።

ክት ልብስሽ ይውጣ ፤ ፊትሽ ይሁን ፋኖስ
ልበሽ የድል ካባ...
ለማን ብለሽ መድከም ፤ ለምን ብለሽ ማነስ?።

ሲደክምሽ በርትቶ ፤ ሲበርድሽ የሞቀው
ደስ ያለሽ ቀን ነው፤
የሞላልሽ ቀን ነው ፤ መግቢያው የሚጨንቀው።


እኔን ባይ



@yegtmmedbl
@yegtmmedbl
@yegtmmedbl
280 views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 21:26:23 ደና ሁኚ አለም በቅርብ ቀን………

እፁብ ዘመቻ

join US @et12sub
@et12sub
294 views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 20:28:02 ሲኦል ላይ ቅጠሪኝ

እፁብ ዘመቻ


የቀጠርኩሽ ጊዜ የምትቀጥሪኝ ቀን፣
ቀኑ አመት ያህል እልፉኝ ሲርቀን።
በናፉቆት ወላፈን በፉቅር ፉም እሳት፣
አልሄድም ስትቀጥረኝ አትመጣም ስቀጥራት።

እኔ ምቀጥርሽ ቀን፣
ይጎላል ያንቺ ቀን።
ምክንያትሽ ይበዛል እኔጋ እንዳትመጪ፣
ባይኔ ባላይሽም ከልቤ አትወጪ።
የቀጠርኩሽ እለት እንቅፋት አያጣሽ፣
መጣው በሚለው ቃል ልቤን እየቀጣሽ።


አንቺ ምቀጥሪኝ ቀን፣
ይጎላል የኔ ቀን።
እገሌ ይሞታል ቀብር እደርሳለው፣
አንቺን እያሰብኩኝ ለሟች አለቅሳለው።
እገሊት አግብታ ለሰርግ ይጠሩኛል፣
በነሱ ቀጠሮ አንቺን ያሳጡኛል።

እኔ ምቀጥርሽ ቀን፣
ይጎላል ያንቺ ቀን።
ሽርጉድ ይበዛል ከቤት እንዳትወጪ፣
እኔም እሄዳለው አንቺ ስትመጪ።
ጫማሽ ይበጠሳል በድንገት ያምሻል፣
የቀጠረሽ ልቤ ፈልጎ ያጣሻል፣
የናፈቀሽ አይኔ ሳያይሽ ይመሻል።


አንቺ ምቀጥሪኝ ቀን፣
ይጎላል የኔ ቀን።
እጄ ባዶ ይሆናል አበዳሪ አጣለው፣
ባካል ባላገኝሽ ባሳብ አይሻለው።
መምጫ ታክሲ አጥቼ በግሬ እኳትናለው፣
ዳሩ ምን ያደርጋል ስደርስ አጣሻለው።

እናም የኔ ናፉቆት……

ስትቀጥሪኝ ስቀጥርሽ እንዲህ ማንገናኝ ፣
ምን አልባት ፈጣሪ አልፈቀደ ይሆናል።
በምድር ቀጠሮ በምድር ጥበቃ፣
በኔና አንቺ ፉቅር ናፉቆት ነው አለቃ።

እናም ውዴ ገላ፣
ልስጥሽ አንድ መላ።


ሞት ያለቀጠሮ ፉቀጅ እንዲመጣ፣
አንቺም እንድቀጥሪኝ እኔም እንድመጣ።
ወደ ሞት ቀጠሮ ወደ ማንቀርበት፣
ነብስሽን ወስደሻት ነብሴን ቅጠሪበት።

እናም የኔ ናፉቆት………

ለጥፋቴ ፉርጃ ለሀጥያትሽ ቅጣት፣
ነብስሽን በእሳት እግዜሩ ሲቀጣት፣
ሲኦል ላይ ቅጠሪኝ እኔም እንድመጣ፣
አንቺን እንዳገኝሽ ፈጣሪዬን ሳጣ።


እፁብ ዘመቻ

join and ሼር

@et12sub
@et12sub
285 views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 06:32:56
@Habteshart
@Habteshart
Join us
284 views03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ