Get Mystery Box with random crypto!

ስትናፉቀኝ ምን ላርግ?? እፁብ ዘመቻ አንተ ስናፉቀኝ…… እንዳላንጎራጉር በትዝታ ዜማ፣ | ethioግጥም(የእፁብ ግጥሞች)✍✍✍

ስትናፉቀኝ ምን ላርግ?? እፁብ ዘመቻ


አንተ ስናፉቀኝ……
እንዳላንጎራጉር በትዝታ ዜማ፣
ሀላፊው አግዳሚው ይህ ጉዴን ከሰማ፣
እሬሳ ናፈቀች አበደች እያሉ፣
ከንፈር መጣጭ መስለው ልቤን ያደማሉ።


በምታምነው አምላክ፣
ስናፉቀኝ ምን ላርግ?

ላንተ እንዳልተነፉስ የናፉቆቴን ሲቃ፣
ጆሮህ ከኔ ርቋል አይሆነኝ ጠበቃ።
አይኖችህ ላያዩኝ በናፍቆት ስቀጣ፣
መናፈቄ በዛ አንተ ላትመጣ።
ልብህ እኔን ትቶ ሲገባ ካፈሩ፣
ምነው ይህ ናፍቆትህ አለመቀበሩ?

ምን ላርግ ስትናፍቀኝ?
ሰመመን ገደለኝ።

አፈርህን ምሼ ከመቃብርህ ስር፣
ጮኬ እጣራለው ትሰማ ይመስል።
የአላዘር ሞትን ቢሰጥህ ምን አለ፣
ውስጤን ባሳምነው ትንሳዬህ እንዳለ።

በምታምነው አምላክ ፣
ስትናፉቀኝ ምን ላርግ?

አንተ እያለህ የነበሩ፣
ዛሬ ባጣህ ምነው ቀሩ?
ሰሚ የለኝ ማማክረው፣
ምናፍቅህ ብቻዬን ነው።

እኔማ፦
ከሞተው ባላንስም፣
ካለው ስነፃፀር፣
ተንቀሳቃሽ እሬሳ ነኝ፣
ያንተ ናፉቆት የገደለኝ።
ምነው ሞት ሀያሉ ቦታ ቢቀይረኝ፣
እኔን ይዞ ቢሄድ አንተን ከሚነጥቀኝ።

በምታምነው አምላክ ፣
ስትናፍቀኝ ምን ላርግ?

ትትሳዬህን ብጠብቀው እንደቃሉ፣
አበድሽ አሉ ያዩኝ ሁሉ።
ቅሉ ምኔ ያደርጉት ፣
የናፍቆትን ቅጣት፣
ኬት አውቀው መች አዩት።


የናፈቁትን ሰው ማግኘት ከተቻለ ፣
አንተ ወራጅ ውሀ ብትሰጠኝ ምን አለ።
ሞትህን ባምነውም ትነሳ ይመስል፣
ጮኬ እጣራለው ከመቃብርህ ስር።


ምላርግ ስናፉቀኝ?
አንዴ ተለመነኝ?
እመጣለው በለኝ።

እግዜሩን አሎቅሰው ስራው ለበጎ ነው፣
አንተን የወሰደህ እኔን ለማኖር ነው።
የሄደን ሚያስረሳ መፉትሄማ ካለ፣
እኔም እንድረሳው ብትነግሩኝ ምን አለ።

ምን ያህል ቅጣት ነው ምንኛ መጎዳት?
በማያገኙት ሠው በናፉቆት መቀጣት።

አንዴ ተለመነኝ፣
ጆሮህን አውሰኝ፣
በምታምነው አምላክ፣
ስትናፉቀኝ ምን ላርግ??

እፁብ ዘመቻ join Us
@et12sub