Get Mystery Box with random crypto!

ሲኦል ላይ ቅጠሪኝ እፁብ ዘመቻ የቀጠ | ethioግጥም(የእፁብ ግጥሞች)✍✍✍

ሲኦል ላይ ቅጠሪኝ

እፁብ ዘመቻ


የቀጠርኩሽ ጊዜ የምትቀጥሪኝ ቀን፣
ቀኑ አመት ያህል እልፉኝ ሲርቀን።
በናፉቆት ወላፈን በፉቅር ፉም እሳት፣
አልሄድም ስትቀጥረኝ አትመጣም ስቀጥራት።

እኔ ምቀጥርሽ ቀን፣
ይጎላል ያንቺ ቀን።
ምክንያትሽ ይበዛል እኔጋ እንዳትመጪ፣
ባይኔ ባላይሽም ከልቤ አትወጪ።
የቀጠርኩሽ እለት እንቅፋት አያጣሽ፣
መጣው በሚለው ቃል ልቤን እየቀጣሽ።


አንቺ ምቀጥሪኝ ቀን፣
ይጎላል የኔ ቀን።
እገሌ ይሞታል ቀብር እደርሳለው፣
አንቺን እያሰብኩኝ ለሟች አለቅሳለው።
እገሊት አግብታ ለሰርግ ይጠሩኛል፣
በነሱ ቀጠሮ አንቺን ያሳጡኛል።

እኔ ምቀጥርሽ ቀን፣
ይጎላል ያንቺ ቀን።
ሽርጉድ ይበዛል ከቤት እንዳትወጪ፣
እኔም እሄዳለው አንቺ ስትመጪ።
ጫማሽ ይበጠሳል በድንገት ያምሻል፣
የቀጠረሽ ልቤ ፈልጎ ያጣሻል፣
የናፈቀሽ አይኔ ሳያይሽ ይመሻል።


አንቺ ምቀጥሪኝ ቀን፣
ይጎላል የኔ ቀን።
እጄ ባዶ ይሆናል አበዳሪ አጣለው፣
ባካል ባላገኝሽ ባሳብ አይሻለው።
መምጫ ታክሲ አጥቼ በግሬ እኳትናለው፣
ዳሩ ምን ያደርጋል ስደርስ አጣሻለው።

እናም የኔ ናፉቆት……

ስትቀጥሪኝ ስቀጥርሽ እንዲህ ማንገናኝ ፣
ምን አልባት ፈጣሪ አልፈቀደ ይሆናል።
በምድር ቀጠሮ በምድር ጥበቃ፣
በኔና አንቺ ፉቅር ናፉቆት ነው አለቃ።

እናም ውዴ ገላ፣
ልስጥሽ አንድ መላ።


ሞት ያለቀጠሮ ፉቀጅ እንዲመጣ፣
አንቺም እንድቀጥሪኝ እኔም እንድመጣ።
ወደ ሞት ቀጠሮ ወደ ማንቀርበት፣
ነብስሽን ወስደሻት ነብሴን ቅጠሪበት።

እናም የኔ ናፉቆት………

ለጥፋቴ ፉርጃ ለሀጥያትሽ ቅጣት፣
ነብስሽን በእሳት እግዜሩ ሲቀጣት፣
ሲኦል ላይ ቅጠሪኝ እኔም እንድመጣ፣
አንቺን እንዳገኝሽ ፈጣሪዬን ሳጣ።


እፁብ ዘመቻ

join and ሼር

@et12sub
@et12sub