Get Mystery Box with random crypto!

የሽርክ አይነቶች ስንት ናቸዉ?? ሽርክ ሁለት ክፍሎች አሉት እነሱም ፦ትልቁ ሽርክ እና | ᎷUᏚᎯᏰ™ Islamic Page

የሽርክ አይነቶች ስንት ናቸዉ??

ሽርክ ሁለት ክፍሎች አሉት

እነሱም ፦ትልቁ ሽርክ እና
ትንሹ ሽርክ በመባል ይታወቃሉ።

❶.ትልቁ ሽርክ

➱ትልቁ ሽርክ ከኢስላም የሚያስወጣ እና ባለቤቱ ወደ አላህ በተዉበት ሳይመለስ ከሞተ በእሳት ዉስጥ ዝንተ አለምእንዲዘወትር የሚያረግ ትልቅ ወንጀል ነዉ።
➲ይህም አምልኮት (ኢባዳ)ከአላህ ዉጭ ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት ነዉ።
ለምሳሌ፦
➢ለእከሌ ብሎ ዱዓ ማረግ
➢ለእከሌ ብሎ ማረድ
➢የሞተን ሰዉ ይጠቅመኛል ወይም ይጎዳኛል ብሎ ማመን
➢ፉጡራን በማይችሉት ነገር መለመን እና ድረሱልኝ ማለት ወ.ዘ.ተ......

❷ትንሹ ሽርክ

➱ትንሹ ሽርክ ከኢስላም ባያስወጣም ተዉሂድን ያጎላል፤ወደ ትልቁ ሽርክም ሊያደርስ ይችላል።

ይህ የሽርክ ክፍል በሁለት ይከፈላል እነሱም፦

⓵በንግግር እና በተግባርም ግልፅ የሆነዉ። ለምሳሌ፦ ➤ከአላህ ዉጭ በሆነን አካል መማል ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ብለዋል።

➫ከአላህ ዉጭ በሆነ አካል የማለ ሰዉ በእርግጥም ክዷል (አጋርቷል) ቲርዝይ ተግቦታል

➤አላህ እና እንትና (ስለ ፈለጉ)ነዉ እንዲህ የሆንኩት ብሎ ማለት።

ቲርሚዚይ በዘገቡት ሀዲስ
<<ለነብዩ "አላህ እና አንተ ስለፈለጋችሁ ነዉ" ሲሏቸዉ፤ እንዲህ አሉ "ለአላህ ባላንጣ ታድርገኝ አለን? አላህ ስለፈቀደዉ ብቻ በል"።>>

⓶ድብቅ ሽርክ፦የትንሽ ሽርክ ክፍል ሲሆን ስራዎችን ለይዩልኝ እና ይስሙልኝ መከወን ነዉ።
ለምሳሌ ፦
➢የሰዎችን አድናቆት በመከጀል ሰደቃ መስጠት
➢ሰላትን ማሳመር ለይዉልኝ ብሎ
➢ቁርአን ቢቀሩ ድምፅን ማሳመር ወ.ዘ.ተ ......

ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ብለዋል።

➫በጣም ከምፈራላችሁ ነገር ትንሹ ሽርክ ነዉ። ትንሹ ሽርክ ምንድን ነዉ? ተብለዉ ሲጠየቁ "ሪያዕ(ይዩልኝ እና ይስሙልኝ)ነዉ" በማለት መለሱ። በዃሪ ዘግቦታል

ሁላችንም ከሁለቱም ሽርክ እንጠንቀቅ ሌሎችንም እናስታውስ

ተውሂድ የተፈጠርንበት አላማ ነው !!
ሁል ግዜም ተውሂድ ይቀድማል

@Islamic_direction