Get Mystery Box with random crypto!

የትግራይ ሀይሎች አላማጣ ከተማ አቅራቢያ ተቆጣጥረዋቸው ከነበሩ መንደሮች ለቀው መውጣታቸውን አቶ ጌ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የትግራይ ሀይሎች አላማጣ ከተማ አቅራቢያ ተቆጣጥረዋቸው ከነበሩ መንደሮች ለቀው መውጣታቸውን አቶ ጌታቸው አስታወቁ

የትግራይ ሀይሎች በአላማጣ ከተማ አቅራቢያ ከሚገኙ “ገርጃሌ” እና “በቅሎ ማነቂያ” ከተባሉ መንደሮች ለቀው መውጣታቸውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አስታወቁ።

የትግራይ ሀይሎች ከመንደሮቹ ለቀው እንዲወጡ የተደረገው ከፌደራል መንግስቱ እና ከአማራ ክልል መንግስት ጋር የተደረሰውን መግባባት በማክበር መሆኑን አቶ ጌታቸው ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ከአከባቢው ተፈናቅለው የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማስቻል ሁኔታዎችን ለማመቻችት መሆኑን ገልጸዋል። በረካታ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለሱ ስራ በሂደት ላይ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ በማህበራዊ ሚዲያ ኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አመላክተዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1