Get Mystery Box with random crypto!

ነገ በተወሰኑ የከተማዋ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቋረጣል ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ነገ በተወሰኑ የከተማዋ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቋረጣል

ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደሚቋረጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

በዚህም በቦሌ አትላስ፣ ደሳለኝ ሆቴል፣ ሲቪል ሰርቪስ፣ ፊጋ፣ ላምበረት፣ አንቆርጫ፣ የተባበሩት፣ ፍየል ቤት፣ ገዳመ እየሱስ ቤተ ክርስቲያን፣ ጭላሎ፣ ኮካ፣ አዲሱ ገበያ እና አካባቢዎቻቸው የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉና በከፊል ይቋረጣል ተብሏል።

በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ደንበኞች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1