Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ትልቅ ሀገር ውስጥ የሀገሩ ንጉስ ነበር እና እዚህ ሀገር ውስጥ ይሄ ንጉስ ያስለመዳቸው አንድ | 🦋እራስን ፍለጋ🦋🦋67

አንድ ትልቅ ሀገር ውስጥ የሀገሩ ንጉስ ነበር እና እዚህ ሀገር ውስጥ ይሄ ንጉስ ያስለመዳቸው አንድ ነገር አለ በየአመቱ እጣ የወጣለት የጠየቀውን ሁሉ ይደረግለታል እና ይሄ እጣ ደርሶ ለአንድ ሰው ወቶለት ሰውየውም በሚሊየን የሚቆጠር ብር ጠይቆ እንደጥያቄው ብር ተሰጠው።

በሌላኛው አመት እንደዚ እጣ ወቶ ለአንድ ሴትዮ ይደርሳታል ይቺ ሴት የፈራረሰ ቤት ውስጥ የምትኖር ወደ ቤቷ እንኳን ለመሄድ መንገዶቹ የፈራረሱ ናቸው የንጉሱም ጠባቂዎች ንጉሱ ምን እንዲያደርግልሽ ትፈልጊያለሽ አሏት?

ሌሎች ሰዎች መኪና ይሏት ጀመር ሌሎች ደሞ አንቺ ደሀ ነሽ ቤትሽ የፈራረሰ እና ጭቃ ነው ስለዚህ ብዙ ብር ጠይቂ እና በብሩ ቤትም ግዢ አሏት ነገር ግን ልጅቷ አስተዋይ እና ብልህ ነበረች ማንንም አልሰማችም ለንጉሱ ጠባቂዎች እኔ ምፈልገው ነገር አለ አለች ንጉሱ ወደ ቤቴ ይግባ ጠባቂዎች ደነገጡ እንዴት ብትደፍሪ ነው ንጉሱን የፈራረሰ ቤትሽ ውስጥ የተከበሩትን ንጉስ የምጠሪው በማለት ሊመቷት ሞከሩ ንጉሱ ግን በታላቅ ድምፅ እንዳይነኳት ተናገሩና ንጉሱ ላያደርግ ቃል አይገባምና ልጂቱ የወደደችውን ይደረግላታል እኔም እገባለው ቤቷንም ለንጉስ እንዲመች አድርጋቹ ስሩት በማለት አዘዙ የንጉሱም ጠባቂዎች ቤቷን ለንጉሱ እንዲመጥን አርገው ከተማ የሚያክል ቦታ ላይ በጣም ትልቅ ቤት ውስጡ ውጪው በወርቆች የተከበበ መንገዶች በአልማዝ በብር ያጌጡ ሆነው ተሰሩላት የዚህ ሁሉ ምክንያት ወደ ውስጥ የሚገባው የከበረ ስለሆነ ነው።

ታዲያ ይሄን ሁሉ ለምን አወራ ካላቹኝ በምንም አይነት ድካም ውስጥ ብትሆኑ ሀጥያት ውስጥ ብትሆኑ የአይሁድ አንበሳ የነገስታት ንጉስ #ኢየሱስን ወደ ውስጣቹ ጥሩት አስገቡት #ኢየሱስ ለእራሱ እንዲመች አድርጎ ይሰራቸዋል።

ትኩረት_ሁሉ_ወደ_ኢየሱስ
Abeniye bless u
ስላካፈልከን የኔ ቆንጆ በረከት ክፉ አይንካህ

@KOMPANY2141
With @erasnflega