Get Mystery Box with random crypto!

ወጥነት (consistency) ብርድ ነው ብለን እንቅልፍን አንመርጥም። ሠው አይኖርም ብለን ከመን | 🦋እራስን ፍለጋ🦋🦋67

ወጥነት (consistency)

ብርድ ነው ብለን እንቅልፍን አንመርጥም። ሠው አይኖርም ብለን ከመንገዳችን ወደኅላ አንልም።

ሁሌም ለአላማችን እንተጋለን። ለውጥ ሂደት ነው። ቀናት፣ ወራት፣ አመታትን ይፈልጋል። በዚህ ረጅም መንገድ ለመጓዝ የወጥነትን ባህሪ (consistency) ማዳበር ይገባናል። በህይወታቸው የፈለጉትን ያገኙ ሠዎች ትልቁ ባህሪያቸው ወጥነት ነው። የትኛውም ሁኔታ ከሀሳባቸው እንዲያስቆማቸው አይፈቅዱም።

በየትኛውም የህይወት ክፍላችን ላይ (በስራ፣ በግንኙነት፣ በመንፈሳዊነት ወዘተ) ወጥነትን ይኑረን። ያሰብነውን ውጤት እስክናገኝ ድረስ በመንገዱ ላይ እንቆይ። ወጥ እንሁን። (ሙና ጀማል)

መልካም ቀን!

@erasnflega