Get Mystery Box with random crypto!

ልዩነትን ማመን! ፈጣሪ ህልም ሲሰጥህ ፣ ባለራዕይ ሲያደርግህ ፣ ለትልቅ ስፍራ ሲመርጥህ ፣ ሲያ | ቁምነገር

ልዩነትን ማመን!

ፈጣሪ ህልም ሲሰጥህ ፣ ባለራዕይ ሲያደርግህ ፣ ለትልቅ ስፍራ ሲመርጥህ ፣ ሲያጭህ ህልም ብቻ አይሰጥህም ፣ ራዕይ ብቻ አያስታቅፍህም ፤ እኩል በእኩል የምትቀበለው የልዩነት ህመም ይሰጥሃል ። ህመሙ ድውይ የሚያደርግህ ሳይሆን የሚፈውስህ ነው ፤ ህመሙ ጊዜያዊ እንጂ ጠላቂ አይደለም ፤ ህመሙ የሚሰራህ እንጂ የሚያፈርስህ አይደለም ።

አዎ! ማለም ቀላል ቢሆን ሁሉም ህልመኛና ባለራዕይ በሆነ ነበር ፤ ማለም ልዩነት ባይፈልግ ሁሉም አንድ ላይ ባለ ትልቅ ህልም ባለቤት በሆነ ነበር ።

አዎ! ጀግናዬ..! የህልመኝነትህ ዋናው ሚስጥር ልዩነትህን ማመንህና የህይወት አላማህን /life purpose/ ማወቅህ ነው ። የተለየህ ስለሆንክ ከሌላው በተሻለ ታልማለህ ፤ ታቅዳለህ ፤ ግብህን ታስቀምጣለህ ፣ ለእርሱም ትለፋለህ ፣ ትተጋለህ ትደክማለህ ። የድካምህ ውጤት ይታይሃል ፤ የህልምህ ጫፍ በጥቃቅን እርምጃዎች /baby steps/ ይደረሳል ፤ ግብህም ከዳር ይደርሳል ።

አዎ! ትልቅ ህልም ስላለህ ነገሮች ላይ ያለህ እይታ ልዩ ነው ፤ አቋምህ ግሩም ነው ፤ እያንዳንዱ እንሽስቃሴህ ድንቅ ነው ። ስትራመድ ፊትለፊትህን ትመለከታለህ ፤ ጎንህን ታስተውላለህ ፤ ጀርባህን ታጤናለህ ። መዳረሻህን ማወቅህ ጉዞህን ያቀለዋል ፤ ከውስጥ መኖርህ ህይወትህን ያጣፍጠዋል ፤ ያሳምረዋል ። ላንተ መኖር ፣ መብላት ፣ መጠጣት ፣ መተኛት ብቻ አይደለም ፤ ላንተ ህይውት ማብላት ፣ ማጠጣት ፣ ማስተኛት ፣ መደገፍ ፣ መርዳትም ጭምር ነው ። ህይወትህ ፣ መኖርህ ሰው ለተራበው ፣ ሰው ላጣው ወገንህ ነው ፤ ልባሽ ጨርቅ ለሌለው ፤ ቁራሽ እንጀራ ለተራበው ፤ ጥሪት ውሃ ለተጠማው ገራገር አምሳያህ ነው ። ግድ የሚሰጥህ ያንተ ድሎት ብቻ አይደለም ፤ የምታስቀድመው ሰው መሆንን ፤ ሰው ማትረፍን ነው ።

አዎ! ማለምህን እንዳታቆም ፤ ከግብህ እንዳትመለስ ፤ ራዕይህን እንዳትተወው ። አስታውስ ህልምህ ያንተ ብቻ አይደለም ፤ ከጀርባው ብዙዎች ይጠብቁታል ፤ ብዙዎች ይናፍቁታል ። ለወገንህ መድረስህ ጉልበት ይሁንህ ፤ ችግሩን ማቅለልህ ሃይል ይሁንህ ፤ ያበርታህ ፤ ያጠንክርህ ። ካንተ በላይ የሚጠብቁህ ቤተሰብ ፤ ዘመድ ፤ ወዳጅ ፤ ጓደኛ ፤ ወገን እንዳለህ አስታውስ ። ቢያንስ አንድን ነፍስ ታደግ ፤ የመኖርን ጠዓም አሳያት ፤ ትልቅ ሁን ፤ ትልቅነትህን ስራህ ይመስክር አምላክም በበረከትን ያብስርህ ።

ቸር ያውለን!!!
@enkopawiyan
@enkopawiyan
@enkopawiyan

@betina21
https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ