Get Mystery Box with random crypto!

ትርፍህ ሰው ነው! በተተከልክ ማግስት ጥላ አትሆንምና ለጊዜው መተከልህ መልካም ነው ። ምንም | ቁምነገር

ትርፍህ ሰው ነው!

በተተከልክ ማግስት ጥላ አትሆንምና ለጊዜው መተከልህ መልካም ነው ። ምንም ደስተኛ ለጊዜው ደስተኛ ባትሆንም በህይወት መኖርህ ትልቁ በረከትህ ነው ። ሰዎችን ለመርዳት እያሰብክ ባታደርገው እንኳን ለጊዜው ማሰብህም በቂ ነው ። ባንተ ድካም ቤተሰቦችህ እንዲያርፉ ብትፈልግም ለጊዜው ፍላጎትህ ከምንም በላይ ነው ። የመታስባቸው መልካም ተግባራት መነሻቸው ሃሳብ ነው ፤ መሰረታቸው ፅኑ ፍላጎት ነው ፤ ቅንነት ነው ፤ ደግነት ነው ። የመልካም ዕሳቤህ መገኛ አንተ ነህ ። ፍላጎትህ የትልቅነትህ ሚስጥር ነው ፤ ሃሳብህ የሰውነትህ ጥግ ነው ። ፍላጎትህ ያለምክንያት አይመጣም ፤ ሃሳብህም በባዶ አልተወለደም ፤ አንድ ቀን እውን መሆኑ አይቀርም ። ደጋግ ልቦች በቅን ሃሳባቸው ብቻ ያርፋሉ ፤ ሰላምን ያገኛሉ ፤ ይረጋጋሉ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ልብ ቀና፣ ደግ አሳቢ ሰው በስብዕናው በአመለካካቱ ብቻ ይደሰታል ። ክፋት የሌላት ልብ በምንም አጋጣሚ ከፍታን ከሌላ ሰው አትጠብቅም ። በመልካምነት መኖር ክፍያ የለውም ፤ ወጪ አያስወጣም ። ለሰው መጨነቅ ፣ ለሰው ማሰብ የሚያጎድልብን ነገር የለም ። አንድ የማናውቀውም ሆነ የምናውቀው ሰው በእኛ ምክንያት በህይወቱ የሆነ ነገር ቢያገኝ ፣ ቢሳካለት ፣ ቢለወጥና ቢያድግ የሙላታችን ምክንያት ይሆንልናል ። ኬትም የማይገኝ የልዩ ደስታ ባለቤት ያደርገናል ።

አዎ! መልካምነት የድንቅ ሰዎች መገለጫ ነው ። ለወገን ደራሽነት ፣ አጋዥነት ፣ አበርታችነት የንፁ ልቦች ስጦታ ነው ። የሰውነትህ ሙሉነት በጓደኛህ ደስታ ስትደሰት ነው ፤ ለቤተሰብህ እድገት በምታደርገው ጥረት ነው ፤ ለወገንህ በምታበረክተው አበርክቶት ነው ። ለእራስ ብቻ መሮጥ የትም አያደርስም ። ትርፍህ ሰው ነው ። ምንም ብትሰራ የሚጠቀመው ሰው ነው ፤ ያንተም ተጠቃሚነት ከሰው ይነሳል ። ብትደክም ፣ ብትለፋ አገልጋይነትህ ለወገንህ ነው ። ምንም እንኳን ለእራስህ ጥቅም ብትለፋ የምትጠቀመው በሰጠሀው አገልግሎት ልክ ነው ።

አዎ! በመልካምነት ተመላለስ ፣ በቅንነት ስራ ፤ ጣፋጩን ስጦታህንም ተቀበል ። በንፉግነትህ ከምታገኘው ገንዘብ በአገልጋይነትህ ፣ በመስጠትህ የምታገኘውን ደስታ እጅጉን የተሻለ ነውና እርሱን ምረጥ ።

ቸር ዋሉልኝ!!!
@enkopawiyan
@enkopawiyan
@enkopawiyan


@betina21

https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ