Get Mystery Box with random crypto!

የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ለመመረቂያ ፅሁፋቸውን ዲፌንስ ዘንጠው ቀርበዋል፡፡ ከመካከላቸው | ቁምነገር

የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ለመመረቂያ ፅሁፋቸውን ዲፌንስ ዘንጠው ቀርበዋል፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ተማሪ ግን በተራ አለባበስ እና በተበጣጠሰች የነጠላ ጫማ ቀረበ፡፡ ለዲፌንስ የተዘጋጁ መምህራን በልጁ ግድ የለሽ አለባበስ ተበሳጭተው ይሰድቡት ይዘልፉት ጀመር፡፡ ዘለፋና ስድባቸውን ከጨረሱ በኋላ እንባ እየተናነቀው መናገር ጀመረ፡፡
’’እኔ የዲግሪ መመረቂያ ፅሁፌን ለማቅረብ እዚህ ከፊታችሁ የቆምኩት በፈጣሪ ተዓምር ነው፡፡ አቅሜ በፈቀደው ልክ በጥሩ አለባበስ ቀርቤያለሁ፡፡
ቤተሰቦቼ በጣም ባለፀጋ ነበሩ የ9 አመት ልጅ አና የ4ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ፡፡ ከሁለት እህቶቼ ጋር ብቻችንን ቀረን የአባቴ ታናሽ ወንድም አጎታችን ለተወሰኑ አመታት ከቤቱ ካስጠለለን በኋላ የቤተሰቦቻችንን ሀብት እና ንብረት በመውረስ ከቤቱ አባረረን፡፡ ሳገኝ እየሰራሁ ሳጣ እየለመንኩ እህቶቼን እና እራሴን መመገብ ጀመርኩ በዚህ ሁኔታ እያለን እኔና እህቶቼ የተሻለ ትምህርት በመማር ህይወታችንን መቀየር እንዳለብን ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡ ግማሽ ቀን ከሰው ማሳ ላይ እያረስኩኝ እህቶቼን እመግባለሁ ግማሽ ቀን የግንባታ ስራ እየሰራሁ አስተምራቸዋለሁ፡፡ እግዚአብሄር ይመስገን እስካሁን ቃሌን ለመጠበቅ ችያለሁ ፡፡ እኔ በዲግሪ ልመረቅ ነው እህቶቼንም ኮሌጅ አስተምራለሁ፡፡ ዛሬ እንደጓደኞቼ ዘንጬ ለመምጣት አስቤ ነበር፡፡ እህቶቼ የሴሚስተር የትምህርት ክፍያ ተጠይቀው ለሱፍ እና ለጫማ ያዘጋጀሁትን ገንዘብ ለነሱ ትምህር ለመክፈል ተገደድኩ…’’ ከፊቱ ተቀምጠው ሲዘልፉት የነበሩ መምህራን አንገታቸውን ደፉ ከመምህራኑ መካከል አንዷ ’’እባክህ ከዚህ በላይ አትናገር ለመስማት የሚሁን ጥንካሬ የለኝም’’ አለች እንባ እየተናነቃት፡፡
ተማሪው የመመረቂያ ዲፌንሱን በሚገባ ተወጣ፡፡ ሳይረዱት የዘለፉት መምህራኖች ከመቀመጫቸው ተነስተው አጨበጨቡለት፡፡ መፅሀፍን በሽፋኑ ሰውን በአለባበሱ አንዳኘው…

@Enkopawiyan
@Enkopawiyan
@Ahadukumneger
ቁምነገር Tube / subscribe