Get Mystery Box with random crypto!

መርዝ ምንድነው አንድ ሰው ለጠየቀው ጥያቄ ሩሚ የሰጠው መልስ ? መርዝ ምንድነው? ሩሚ የሰጠው መል | ቁምነገር

መርዝ ምንድነው
አንድ ሰው ለጠየቀው ጥያቄ ሩሚ የሰጠው መልስ ?
መርዝ ምንድነው?
ሩሚ የሰጠው መልስ ውብ ነበር?
ማንኛውም ከሚያስፈልገን መጠን በላይ የሆነ ነገር ሁሉ መርዝ ነው። ስልጣን ፣ ሀብት፣ ድህነት፣ ንዴት፣ ስግብግብነት፣ ስንፍና፣ ጥላቻ ፣ ራስ ወዳድነት፣ ፍቅር፣ ጉጉት፣ ወይንም ሌላ ማንኛውንም ነገር ሊሆን ይችላል።

ፍርሃት ምንድነው?
እርግጠኛ አለመሆንን አለመቀበል ነው። እርግጠኛ አለመሆናችንን ብንቀበል ፣ ፍርሃት ገድል ይሆናል።

ቅናት ምንድነው?
የሌሎችን በጎ ነገር አለመቀበል ነው። የሌሎችን በጎነት ብንቀበል ፣ መነሳሳት ይፈጥርልናል ።

ንዴት ምንድነው?
ከቁጥጥራችን ውጪ የሆኑ ነገሮችን አለመቀበል ነው። ያንን ብንቀበል ትእግሥት ይሆነናል።

ጥላቻ ምንድነው?
ጥላቻ አንድን ሰው እንዳለ በሰውነቱ መቀበል አለመቻል ነው። አንድን ሰው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል ብንችል ግን፣ ያ ጥላቻ ፍቅር ይሆናል
መልካም ዛሬ

@Enkopawiyan
@Enkopawiyan
ቁም ነገር tube/ subscribe @Ahadukumneger