Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ education_ministry — የትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ education_ministry — የትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @education_ministry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.42K
የሰርጥ መግለጫ

This is ministry of education's official Telegram channel.

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-26 22:23:01 ###

የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በ2015 ዓ.ም ይጀምራል።

የሙከራ ትግበራው በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ሥርዓተ ትምህርቱ ሀገር በቀል እውቀት፣ ግብረ ገብ እንዲሁም ሳይንስና ቴክኖሎጂን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

በሙከራ ትግበራው የሚገኙ አስተያየቶች ተካተው ሥርዓተ ትምህርቱ በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ ይሸጋገራል ተብሏል።
https://t.me/education_ministry
1.2K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 14:50:11 የ 12ኛ ክፍል ፈተና በ 2ት ዙር ይሰጣል።

1ኛ ዙር---Social Science ከ መስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3

2ኛ ዙር ---Natural Science ከ ጥቅምት 8 እስከ 11

በዚህ አመት 984,000 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፈል ፈተናን ይወስዳሉ።

Social Science .......622,739 ናቸው።

Natural Science.....361,279 ናቸው።

https://t.me/education_ministry
5.0K views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 12:29:09 " አዲሱ ስርዓተ ትምህርት "

የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ክልሎች አስፈላጊ መፅሀፍትና ቋንቋ የመተርጎም ስራ እየሰሩ ሲሆን በፍጥነት ወደ መፅሀፍ የማሳተም ስራ እንዲገባ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዚህም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት (ኤለመንተሪ) ካሪኩለም ስራ ላይ ይውላል።

በተመሳሳይ በቀጣይ ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ካሪኩለም የሙከራ ስራ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሞከር ሲሆን 2016 ዓ/ም ላይ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

https://t.me/education_ministry
2.8K views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 17:45:08 #የ12ኛ_ክፍል_ብሔራዊ_ፈተና

የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ምክክር ሲካሄድ ውሏል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ከየክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች እና የፈተና ጉዳይ አስፈጻሚዎችና ከትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ባለሙያዎች ጋር በፈተናው አሰጣጥ ላይ ምክክር ማካሄዱን አሳውቋል።

በውይይቱ ላይ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሠነዱ ዙርያ የተለያዩ አስተያቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው ግልጽነትና የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሁሉ ከሚመለከታቸው ባለሚና አካላት ጋር በመሆን እየተከናወነ እንደሚገኝ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

https://t.me/education_ministry
3.2K views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 11:24:37 ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው ዓመት 2015 ትምህርት ዘመን የሚጀምረውን የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የአፈፃፀም መመሪያን በማጸደቅ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማሰራጩት ይታወቃል።

ለመሆኑ መመሪያው ምን ይላል ?

- የመውጫ ፈተናው የመጀመሪያ ዲግሪ የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ይመለከታል።

- መመሪያው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ከሚከወኑ የማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ ነው።

- የመውጫ ፈተናውን ወስዶ 50 በመቶ ውጤት ማምጣት ያልቻለ ተማሪ መመረቅም ሆነ ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ የዲግሪ ሰርተፊኬት ማግኘት አይችልም።

- በመውጫ ፈተና 50 በመቶ ማምጣት ያልቻለ ተጨማሪ ጊዜ ወስዶ በአግባቡ አጥንቶ ፈተናውን 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አምጥቶ ማለፍ እንዲችል ለሁለት ተጨማሪ ጊዜ የመፈተን እድል ይሰጠዋል። ተፈታኙ እድሉን መጠቀም ያለበት የመጀመሪያውን ፈተና ከወሰደ በ3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው።

- አንድ ተማሪ ለምርቃት ብቁ የሚሆነው የመውጫ ፈተናውን ካለፈ ብቻ ሲሆን 3 ጊዜ ተፈትኖ የማለፊያ ነጥብ ያላገኘ ተፈታኝ ከብሄራዊ የብቃት ማዕቀፍ ተገቢው ማስረጃ ይሰጠዋል።

- የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና እንደየትምህርት ፕሮግራሙ ባህሪ በዓመት ሁለቴ እና ከዛም በላይ ሊሰጥ ይችላል።

- የመውጫ ፈተና የሞያ ማህበራት ተጠናክረው የሞያ ፍቃድ ፈተና መስጠት እስከሚጀምሩ በትምህርት ሚኒስቴር ወይም ውክልና በሚሰጠው ተቋም ይዘጋጃል።

መውጫ ፈተና ላይ ሚካተቱ ኮርሶችን በተመለከተ በመጪው ጊዜ በየትምህርት መስኩ በሚዘጋጁ የማስፈፀሚያ ዝርዝር መመሪያዎች ይለያል መባሉንv ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ካሰራጨመው ዘገባ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

https://t.me/education_ministry
3.1K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 10:38:15 #MoE

" የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲሰጥ ታቅዷል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2ዐ14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ
#በሁለት_ዙር እንዲሰጥ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለ42 ዩኒቨርሲቲዎች በተላከውን እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትክክለኛነቱን ባረጋገጠው ደብዳቤ መመልከት ችለናል።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዩኒቨርስቲዎች ፦

1. ምንም አይነት የመደበኛ ተማሪ በግቢ እንዳይኖር እንዲያደርጉ፤

2. በቀጣይ በሚገለጸው ተማሪ ቁጥር ልክ ምግብ እንዲቀርብ ዝግጅት እንዲያደርጉ፤

3. ለፈተናዎች ማቆያ ቦታ አንዲዘጋጅ እና

4. የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በፕሬዚዳንት የሚመራ ዋና ግብረ-ኃይልና በየካምፓሶቹ በዲን /ካምፓስ ኃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ-ኃይል እንዲያደራጁ መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የ2ዐ15 የአካዳሚክ ካላንደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወቅት (ከመስከረም 28 - ጥቅምት 17) ታሳቢ በማድረግ እንዲያዘጋጁ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳስበዋል።

https://t.me/education_ministry
3.2K views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 19:29:23 " አዲሱ ስርዓተ ትምህርት "

የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ክልሎች አስፈላጊ መፅሀፍትና ቋንቋ የመተርጎም ስራ እየሰሩ ሲሆን በፍጥነት ወደ መፅሀፍ የማሳተም ስራ እንዲገባ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዚህም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት (ኤለመንተሪ) ካሪኩለም ስራ ላይ ይውላል።

በተመሳሳይ በቀጣይ ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ካሪኩለም የሙከራ ስራ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሞከር ሲሆን 2016 ዓ/ም ላይ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

https://t.me/education_ministry
2.5K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 10:48:03 #NationalExam

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ ይሰጣል።

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ፈተናው ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የፈተና ደንብ ጥሰቶች
#በህግ ያስጠይቃሉም ተብሏል።

የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጀ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ከቀናት በፊት መገለፁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው።

https://t.me/education_ministry
5.7K views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 23:13:02 የ2015 ትምህርት ዘመን የትምህርት ካላንደር

* በክፍል ውስጥ የመደበኛ ትምህርት መስከረም 9/ 2015 ይጀምራል።

* የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና (ሚንስትሪ) ከሰኔ 5 - 9/ 2015 ዓ.ም ይሰጣል።

* የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከግንቦት 21 - 25/ 2015 ዓ.ም ይሰጣል።

* ሰኔ 30/ 2015 ዓ.ም የዓመቱ ትምህርት ማጠናቀቂያ ይሆናል።

መልካም የትምህርት ዘመን !!


የአዲስ አበባ ከተማ ት/ቢሮ

https://t.me/education_ministry
3.5K views20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 23:11:43 #Reminder

#National_Exit_Exam

በመጪው 2015 ዓ/ም መጨረሻ ላይ የመውጫ ፈተና መሰጠት ይጀምራል።

በ2015 ዓ.ም መጨረሻ መተግበር በሚጀምረው የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዙሪያ ከሰሞኑን የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለአዲስ ዘመን ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ሚኒስትር ዴኤታው ካነሳሷቸው ሃሳቦች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው

• የመውጫ ፈተና ምዘና የሚሰጠው ለመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ብቻ ነው።

• በግልም ሆነ በመንግስት የትምህርት ተቋም የሚማር ተማሪ ዲግሪውን የሚያገኘው ምዘናውን ሲያልፍ ብቻ ነው፡፡

• የመውጫ ፈተናው የሚዘጋጅበት፣ የሚያዝበት እና የሚሰራጭበት ስርዓት ከሰው ንክኪ ነጻ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

• በየዓመቱ ከ150 እስከ 180 ሺህ በመጀመሪያ ዲግሪ የሚመረቁ ተማሪዎችን ምዘና ለመስጠት የሚያስችል አቅም አለ፡፡

• የሙያ ማኅበራት አቅማቸው ሲጎለብት የሙያ ፈተና ይሰጣሉ፤ የመውጫ ፈተና ሥራን ከመንግስት ይረከባሉ።

• ፈተናውን የሚያሰናዱ ተቋማትና መምህራን ዝግጅት ሥራዎች እስከ ግንቦት 2015 ዓ.ም ይሰራሉ፡፡

• የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ግልጸኝነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እየተሰራበት ነው።

https://t.me/education_ministry
3.1K views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ