Get Mystery Box with random crypto!

Yhh

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebc_news_now — Yhh Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebc_news_now — Yhh
የሰርጥ አድራሻ: @ebc_news_now
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የተለያዩ በሀገርዊ እና አለማቀፋዊ እንዲሁም ወቅታዊ የሚካሄድ ዘገባዎች የሚቀርብበት ነው።
ሚዛናዊነትና⚖ "ተደራሽነት📲💻📡📺
እኛን ምረጫዎ ያድረጉ
እባክዎ ለወዳጅ ዘመድዎ ያካፍሉ /share /share

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-25 19:09:07
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ ነው
**

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ የክብር ዶክተሬቱን የሚሰጣቸው በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትን እና ያስተማሩትን በተግባር በመኖራቸው እና ሰውን በሰውነቱ ብቻ በማክበራቸው እንደሆነ ገልጿል።

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ደግሞ ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን በስፖርቱ ዓለም በማስጠራት ጀምራ ለኅብረሰተብ ፍቅር እና አንድነት መጎልበት እየተጋች በመሆኑ የክብር ዶክትሬትቱን ሊሰጣት እንደሆነ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል።
663 views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 10:50:31 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ ይሰጣል
********

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የአገልግሎቱ መረጃ እንደሚያመለክተው ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡
2.3K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 21:27:11
የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበር ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ፣ የተመድ ተወካዮች ፣ የሀገራት አምባሳደሮች ከትግራይ ክልል ለፌዴራል መንግስት ደብዳቤ ይዘው ተመልሰዋል።

ከዚህ ቀደም መልዕክተኞቹ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረጉት ውይይት በትግራይ የመብራት፣ የቴሌኮም፣ የባንክ እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን #በፍጥነት ወደነበረበት መመለስ ለትግራይ ህዝብ አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር።

በዚህም የትግራይ ክልልን እያስተዳደሩ ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በዓለማቀፍ ማህበረሰቡ ተወካዮች በኩል ለፌዴራል መንግስት ደብዳቤ ልከዋል።

ደብዳቤው ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ስልክ ፣ ባንክ፣ መብራት እና የመሳሰሉትን ለመመለስ እና አገልግሎት እንዲጀምሩ ለማድረግ ወደ ክልሉ ገብተው ለሚሰሩ አካላት የደህንነት ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው።

በዚህ #የደህንነት_ማረጋገጫ አገልግሎቶችን ወደነበረበት መመለስ ለማስጀመር ምንም አይነት መሰናክል ሊኖር አይገባም ተብሏል።
2.7K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 15:39:08 የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤትን ይፋ አድርጓል።

ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63.9 በመቶ ያህሉ 50 እና ከዛ በላይ ውጤት አምጥተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን አስታውቋል ፡፡

ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63.9 በመቶ የሚሆነ 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ይህም ካለፉት አመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ለውጤቱ መመዝገብ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ ቢሮው ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርባል።
2.8K views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 06:40:13
አትሌታችን ድርቤ ወልተጂ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች

ዛሬ በወንዶችም በሴቶችም ድል ሳይቀናን አልፏል።
ኢትዮጵያ በተለይ በሴቶች ከፍተኛ ድል ያስመዘገበችበት የኦሪገን ዓለም ሻምፒዮና በዚህ አብቅቷል።
2.3K views03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 06:39:59
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በወንዶች 5 ሺሕ ሜትር ውድድር ድል አልቀናቸውም

አትሌት ዩሚፍ ቀጀልቻ በ8ኛ ደረጃ ውድድሩን ሲያጠናቅቅ አትሌት ሰለሞን ባረጋ 12ኛ ሆኗል።

እንዲሁም አትሌት ሙክታር እድሪስ 13ኛ በመሆን ጨርሷል።

የውድድሩ የወርቅ፣ ብር እና ነሀስ ባለድሎች ፦

1ኛ ኖርዌይ
2ኛ ኬንያ
3ኛ ዩጋንዳ
2.0K views03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 20:45:48
ከሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ።

"ከአራት ቀናት በፊት "አቶ" በሚባለው ቦታ ወደ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን የገባው አሸባሪው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን "ሁልሁል" በሚባል ንዑስ ቀበሌ ከተከበበ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ተደምስሷል። ቡድኑ በኤልከሬ ወረዳ አልፎ ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት ከሸኔ ሽብርተኛ ቡድን ጋር ለመገናኘት አልሞ ነበር። አሸባሪው ቡድን ወደ አሰበው ቦታ ሳይደርስ የያዛቸው 13 ተሽከርካሪዎች የተቃጠሉ ሲሆን ይዞት የገባው ትጥቅና ስንቅም ተማርኳል። ለሶስት ቀን በተካሄደው ኦፕሬሽንም ከ100 በላይ የአሸባሪው ቡድን አባላት ተገድለዋል።"

via EliasMeseret
1.8K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 17:25:20
ኢትዮጵያ የግድቡን ሦስተኛ ዙር ሙሌት ለመጀመር ዕቅድ መያዟ እንዳሳሰባቸው አብዱል ፈታህ አልሲሲ ገለፁ

➩ በየሄዱበት ሀገር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጉዳይ በማንሳት የሚታወቁት የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በሳምንቱ መጀመሪያ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር ሰርቢያ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ባደረጉት ንግግር በግብፅ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማስፋት የታላቁ ህዳሴ ጉዳይን ለመፍታት ያስችላል ብለዋል።

➩ ፕሬዝዳንቱ አክለውም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሶስቱ ሀገራት መካከል ሚዛናዊ እና ፍትሃዊ የህግ ስምምነት መኖሩ የኢትዮጵያን የልማት እና የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ከማሳደግ ጎን ለጎን የግብፅን እና የሱዳንን የውሃ መብት ለማስጠበቅ ያስችላል ብለዋል።

➩ ህጋዊ ስምምነት በሌለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የግድቡን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ሙሌት በማጠናቀቅ በያዝነው አመት መጀመሪያ የግድቡን ተርባይን የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ጀምራለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ሦስተኛውን ሙሌትም በመጭው ነሀሴ እና መስከረም ወር ለመጀመር ዕቅድ መያዟ እንዳሳሰባቸው መግለፃቸውን አልሃራም የተባለውን የግብፅ ጋዜጣ ጠቅስ ዶቼቨለ ዘግቧል።
1.8K views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 21:25:35
የቤቶች እጣ የወጣበት የኮምፒዩተር መተግበሪያ በገለልተኛ አካል እንዲመረመር ኢሰመጉ ጠየቀ!

የጋራ መኖሪያ ቤቶች የእጣ መጭበርበርን በተመለከተ እጣው የወጣበት የኮምፒዩተር መተግበሪያ በገለልተኛ አካል እንዲመረመር ብሎም ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ጠይቋል። ሥልጣናቸውን በመጠቀም ያጭበረበሩት ለሕግ ለሕግ እንዲቀርቡም ዛሬ ሀሙስ ሀምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ጉባኤው ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።
1.7K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 21:13:15 ነገ በእነዚህ አካባቢዎች መብራት ይጠፋል

አርብ፣ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ በመካከለኛ የኤሌትሪክ ሃይል ተሸካሚ ላይ የማሻሻያ ሥራ ስለሚከናወን በሚከተሉት አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለሰዓታት የሚቋረጥ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ

በሲቪል ሰርቪስ ፊት ለፊት፣
በሲ ኤሚ ሲ ልዩ ቤቶች፣
በተባበሩት፣
በሲኤሚሲ ሚካኤል እና አካባቢዎች

ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ

በአያት 49 ማዞርያ፣
በአየር መንገድ ቤቶች፣
በአያት 2፣ 3፣ 4 ኮንደሚኒየም፣
በቦሌ አራብሳ እና አካባቢዎቻቸው

በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጉ ተብሏል፡፡

Via:- Al ain
1.6K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ