Get Mystery Box with random crypto!

የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓ.ም | Yhh

የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤትን ይፋ አድርጓል።

ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63.9 በመቶ ያህሉ 50 እና ከዛ በላይ ውጤት አምጥተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን አስታውቋል ፡፡

ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63.9 በመቶ የሚሆነ 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ይህም ካለፉት አመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ለውጤቱ መመዝገብ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ ቢሮው ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርባል።