Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ የግድቡን ሦስተኛ ዙር ሙሌት ለመጀመር ዕቅድ መያዟ እንዳሳሰባቸው አብዱል ፈታህ አልሲሲ ገ | Yhh

ኢትዮጵያ የግድቡን ሦስተኛ ዙር ሙሌት ለመጀመር ዕቅድ መያዟ እንዳሳሰባቸው አብዱል ፈታህ አልሲሲ ገለፁ

➩ በየሄዱበት ሀገር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጉዳይ በማንሳት የሚታወቁት የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በሳምንቱ መጀመሪያ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር ሰርቢያ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ባደረጉት ንግግር በግብፅ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማስፋት የታላቁ ህዳሴ ጉዳይን ለመፍታት ያስችላል ብለዋል።

➩ ፕሬዝዳንቱ አክለውም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሶስቱ ሀገራት መካከል ሚዛናዊ እና ፍትሃዊ የህግ ስምምነት መኖሩ የኢትዮጵያን የልማት እና የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ከማሳደግ ጎን ለጎን የግብፅን እና የሱዳንን የውሃ መብት ለማስጠበቅ ያስችላል ብለዋል።

➩ ህጋዊ ስምምነት በሌለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የግድቡን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ሙሌት በማጠናቀቅ በያዝነው አመት መጀመሪያ የግድቡን ተርባይን የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ጀምራለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ሦስተኛውን ሙሌትም በመጭው ነሀሴ እና መስከረም ወር ለመጀመር ዕቅድ መያዟ እንዳሳሰባቸው መግለፃቸውን አልሃራም የተባለውን የግብፅ ጋዜጣ ጠቅስ ዶቼቨለ ዘግቧል።