Get Mystery Box with random crypto!

Vaginal Douching ምንድን ነው እና በዶቺንግ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች? | Doctor M nursing Home care

Vaginal Douching ምንድን ነው እና በዶቺንግ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች?

ዶውሺንግ የሴት ብልት ጠረንን ለማስወገድ እና ለማፅዳት በውሃ ወይም በተቀላቀለ ፈሳሽ መታጠብ ነው። በአለም ዙሪያ ባሉ ሴቶች መካከል የተለመደ ነው። ብዙውን ጊዜ ኮምጣጤ ከውሃ ጋር ይቀላቀላል, ነገር ግን አንዳንድ አስቀድመው የታሸጉ የዶቺንግ ምርቶች ቤኪንግ ሶዳ ወይም አዮዲን ይይዛሉ።
በጣም ጥቂቶቹ ደግሞ አንቲሴፕቲክስ እና ሽቶዎችን ይይዛሉ።

ዶቺንግ እንደ ማቃጠል እና የቆዳ መቆጣት ያሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችን እንዲሁም በርካታ ውስብስብ ቸግሮችን ሊያስከትል ይችላል። እነዚህ ውስብስብ ችግሮች ለመሸፋፈን የሚሞክሩትን ማናቸውንም ጉዳዮች ለምሳሌ ያልተለመደ ሽታ ሊያባብሱ ይችላሉ።

ሴቶች ዶቺንግ የሚጠቀሙባቸው የተለመዱ ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
- ደስ የማይል ሽታ ለማስወገድ
- እርግዝናን ለመከላከል
- የወር አበባ ደም ከወር አበባ በኋላ ወይም
ከወሲብ በኋላ የወንድ የዘር ፈሳሽ ለማጠብ
- በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለማስወገድ

ነገርግን ዶቺንግ ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ ለአንዱም አይረዳም።

የአሜሪካ የጽንስና የማህፀን ሕክምና ኮሌጅ ሴቶች የዶቺንግ ምርቶችን እንዲጠቀሙ አይመክርም።

የሴቶች ብልት በተፈጥሮ ጤናማ የፒኤች ሚዛን መስጠበቅ ይችላል። ኢንፌክሽነን ለማስቆም እና የቆዳ መቆጣት ለመከላከል በሚረዱ በባክቴሪያ ወይም flora ተሞልቷል።

ያሉትን ጤናማ ባክቴሪያዎች ካስወገዱ ወይም በጣም ከቀነሱ (በዶቺንግ) ችግር ያለባቸው ባክቴሪያዎች ሊበቅሉ ይችላሉ። ይሄም ኢንፌክሽን እና የበለጠ ከባድ ችግሮች ሊያስከል ይችላል።

መቼ ሐኪም ማማከር አለቦውት?
- ሽታ ያለው ፈሳሽ ካለ
- ነጭ ወይም ቢጫ-አረንጓዴ የሆነ
ፈሳሽ ካለ
- ማቃጠል ፣ ማሳከክ እና መቅላት ወይም
እብጠት ካለ
- በግንኙነት ወቅት ህመም ወይም ምቾት
ማጣት ካለ
- በሽንት ጊዜ ህመም ካለ

ለተከታታይ የጤና ነክ መረጃዎች
https://t.me/Doctormhomecare